Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታ​ቸ​ውን አቀኑ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በደ​መ​ናው ታየ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አሮንም ለመላው የእስራኤል ማኅበር ሲናገር ሳለ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ በዚያም የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ላይ ተገልጦ ይታይ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲህም ሆነ አሮን ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በተናገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታቸውን አዞሩ፤ እነሆም የጌታ ክብር በደመናው ታየ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አሮንም ለመላው ማኅበር በተናገረ ጊዜ ፊታቸውን ወደ በረሓው አዞሩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር በደመና ተገለጠ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዲህም ሆነ፤ አሮን ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በተናገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታቸውን አቀኑ፤ እነሆም የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ታየ።

参见章节 复制




ዘፀአት 16:10
12 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፦


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመ​ና​ውም ስድ​ስት ቀን ሸፈ​ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​መ​ናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ገቡ፤ ወጡም፤ ሕዝ​ቡ​ንም ባረኩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለሕ​ዝቡ ሁሉ ተገ​ለጠ።


ሙሴም፥ “ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ቃል ይህ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋል” አለ።


ማኅ​በሩ ሁሉ ግን “በድ​ን​ጋይ እን​ው​ገ​ራ​ቸው” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ተገ​ለጠ።


ቆሬም ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ወደ ምስ​ክሩ ደጃፍ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ተገ​ለጠ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ማኅ​በሩ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከበ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ ደመ​ናው ሸፈ​ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለጠ።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


跟着我们:

广告


广告