Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ያን ጊዜ የኤ​ዶም አለ​ቆች ሸሹ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች መን​ቀ​ጠ​ቀጥ ያዛ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን የሚ​ኖሩ ሁሉ ቀለጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤ የሞዓብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤ የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞዓብ መሪዎች መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የኤዶም መሪዎች ተስፋ ቈረጡ፤ የሞአብም ኀያላን ተንቀጠቀጡ፤ የከነዓንም ሕዝብ ወኔ ከዳቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞአብን ኃያላን መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።

参见章节 复制




ዘፀአት 15:15
24 交叉引用  

የዔ​ሳው ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ የዔ​ሳው የበ​ኵር ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስ​ፍን፥ ኦሜር መስ​ፍን፥ ሳፍር መስ​ፍን፥ ቄኔዝ መስ​ፍን፥


ቆሬ መስ​ፍን፥ ጎቶን መስ​ፍን፥ አማ​ሌቅ መስ​ፍን፤ በኤ​ዶም ምድር የኤ​ል​ፋዝ መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚህ የሓ​ዳሶ ልጆች ናቸው ።


የዔ​ሳ​ውም የመ​ሳ​ፍ​ንቱ ስም በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው፥ በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው፥ በያ​ገ​ራ​ቸ​ውና በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው ይህ ነው፤ ትም​ናዕ መስ​ፍን፥ ዓልዋ መስ​ፍን፥ ኤቴት መስ​ፍን፥


እርሱ ኀይ​ለኛ ሰው ነውና፥ ልቡም እንደ አን​በሳ ልብ ፈጽሞ ይና​ደ​ዳ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አባ​ትህ ጽኑዕ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ስዎች ኀያ​ላን እንደ ሆኑ ያው​ቃሉ።


ከክፉ ቀን ለምን እፈ​ራ​ለሁ? ኀጢ​አት ተረ​ከ​ዜን ከበ​በኝ፤


በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።


ስለ​ዚህ እጅ ሁሉ ትዝ​ላ​ለች፤ ሰውም ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤


ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ራእይ። እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣን ደመና ተቀ​ምጦ ወደ ግብፅ ይመ​ጣል፤ የግ​ብ​ፅም የእ​ጆ​ቻ​ቸው ሥራ​ዎች በፊቱ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ልብ በው​ስ​ጣ​ቸው ይቀ​ል​ጣል።


“ስለ ደማ​ስቆ፤ ክፉ ወሬ ሰም​ተ​ዋ​ልና ሐማ​ትና አር​ፋድ አፈሩ፤ ቀለ​ጡም፤ እንደ ባሕ​ርም ተነ​ዋ​ወጡ፤ ያር​ፉም ዘንድ አይ​ች​ሉም።


እነ​ር​ሱም፦ ስለ ምን ታለ​ቅ​ሳ​ለህ? ቢሉህ አንተ እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ስለ​ሚ​መ​ጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀ​ል​ጣል፤ እጆ​ችም ሁሉ ይዝ​ላሉ፤ ሥጋና መን​ፈስ ሁሉ ይደ​ክ​ማል፤ ከጕ​ል​በ​ትም እዥ ይፈ​ስ​ሳል፤ እነሆ ይመ​ጣል፤ ይፈ​ጸ​ማ​ልም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ባዶና ባድማ ምድረ በዳም ሆናለች፣ ልብ ቀልጦአል፥ ጕልበቶችም ተብረክርከዋል፣ በወገብም ሁሉ ሕማም አለ፥ የሰዎችም ሁሉ ፊት ጠቍሮአል።


ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።


የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፣ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።


ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።


ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።


ከእኔ ጋር የወጡ ወን​ድ​ሞች ግን የሕ​ዝ​ቡን ልብ አስ​ካዱ፤ እኔ ግን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሜ እከ​ተ​ለው ዘንድ ተመ​ለ​ስሁ።


ይህ​ንም ነገር ሰም​ተን በል​ባ​ችን ደነ​ገ​ጥን፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር እርሱ አም​ላክ ነውና ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ከእኛ የአ​ን​ዱም እን​ኳን ነፍስ አል​ቀ​ረም።


ኢያ​ሱ​ንም፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሀገ​ሩን ሁሉ በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል፤ በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ከእኛ የተ​ነሣ ደነ​ገጡ” አሉት።


ሰዎ​ቹ​ንም እን​ዲህ አለ​ቻ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ሪ​ቱን አሳ​ልፎ እንደ ሰጣ​ችሁ ዐወ​ቅሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ን​ተን መፍ​ራ​ት​ን በ​ላ​ያ​ችን አም​ጥ​ት​ዋ​ልና፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ የተ​ነሣ ቀል​ጠ​ዋ​ልና።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።


በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ያሉ የሳ​ኦል ዘበ​ኞ​ችም ተመ​ለ​ከቱ፤ እነ​ሆም፥ ሠራ​ዊቱ ወዲ​ህና ወዲያ እየ​ተ​ራ​ወጡ ተበ​ታ​ተኑ።


跟着我们:

广告


广告