Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 15:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ “ከፍ ከፍ ብሎ ከብሯልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለጌታ ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለጌታ እዘምራለሁ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ከዚህ የሚከተለውን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፦ “ፈረሱንና ፈረሰኛውን ወደ ባሕር በመጣል፥ ክብር የተሞላው ድል ስለ ተጐናጸፈ፥ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያም ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፤ “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።

参见章节 复制




ዘፀአት 15:1
27 交叉引用  

ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው።


ሰዎች ሊሠ​ሩት ከሞ​ከ​ሩት በላይ፥ ሥራው ታላቅ እንደ ሆነ አስብ።


ብዙ ጊዜ አዳ​ና​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በም​ክ​ራ​ቸው አስ​መ​ረ​ሩት፥ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መከራ ተቀ​በሉ።


ልባ​ቸው በመ​ከራ ደከመ፤ ታመሙ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ው​ንም አጡ።


ገለ​ዓድ የእኔ ነው፥ ምና​ሴም የእኔ ነው፤ ኤፍ​ሬም የራሴ መጠ​ጊያ ነው። ይሁዳ ንጉሤ ነው፤


የባ​ሕ​ሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚ​ሰ​በ​ስ​በው፥ በቀ​ላ​ዮ​ችም መዝ​ገ​ቦች የሚ​ያ​ኖ​ረው።


በሌ​ሊት ከልቤ ጋር ተጫ​ወ​ትሁ፥ መን​ፈ​ሴ​ንም አነ​ቃ​ቃ​ኋት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በውኑ ይጥ​ላ​ልን? እን​ግ​ዲ​ህስ ይቅ​ር​ታ​ውን አይ​ጨ​ም​ር​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እጅ​ህን በባ​ሕሩ ላይ ዘርጋ፤ ውኃ​ውም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን፥ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በፈ​ረ​ሰ​ኞ​ቻ​ቸ​ውም ላይ ይመ​ለስ፤ ይሸ​ፍ​ና​ቸ​ውም።”


ሙሴም እጁን በባ​ሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ባሕ​ሩም ማለዳ ወደ መፍ​ሰሱ ተመ​ለሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከእ​ርሱ ሸሹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በባ​ሕሩ መካ​ከል ጣላ​ቸው።


ማር​ያ​ምም አስ​ቀ​ድማ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ምር አለች፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ምር በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጥሎ​አ​ልና።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያን ከሚ​መ​ኩ​ባ​ቸ​ውና ከሚ​ገ​ዙ​ላ​ቸው አማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


ወደ ባሕር የም​ት​ወ​ርዱ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ውስጥ የም​ት​ጓዙ ሁሉ፥ ደሴ​ቶ​ችና በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዲስ መዝ​ሙር ዘምሩ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ስሙን አክ​ብሩ።


በአ​ንቺ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ፤ በአ​ን​ቺም ሰረ​ገ​ላ​ው​ንና በላዩ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን እበ​ት​ና​ለሁ።


የበ​ዓ​ሊ​ምን ስሞች ከአ​ፍዋ አሰ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ስማ​ቸ​ውም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ታ​ሰ​ብም።


እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።


በዚ​ያም ጊዜ እስ​ራ​ኤል በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ይህን መዝ​ሙር ስለ ጕድ​ጓዱ መዘ​መር ጀመሩ፦


አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


跟着我们:

广告


广告