Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ፈርዖን በቀረበ ጊዜ እስራኤላውያን ቀና ብለው ተመለከቱ፤ እነሆ፣ ግብጻውያን ይከታተሏቸው ነበር፤ እነርሱም በታላቅ ፍርሀት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን ከኋላቸው እየመጡ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ ጌታም ጮኹ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እስራኤላውያን ንጉሡና ሠራዊቱ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል መምጣታቸውን አይተው እጅግ ፈሩ፤ እንዲረዳቸውም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዐይናቸውን አነሡ፤ እነሆም ግብፃውያን በኋላቸው ገሥግሠው ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ።

参见章节 复制




ዘፀአት 14:10
23 交叉引用  

የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


“በግ​ብ​ጽም ሳሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አየህ፤ በኤ​ር​ትራ ባሕ​ርም ሳሉ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማህ፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይ​ልን እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ እር​ሱም የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ንን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።


ወዳ​ጆ​ችህ ይድኑ ዘንድ በቀ​ኝህ አድን፥ አድ​ም​ጠ​ኝም።


አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈ​ር​ድ​ል​ኛ​ለህ? ነፍ​ሴን ከክፉ ሥራ​ቸው፥ ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከአ​ን​በ​ሶች አድ​ናት፥


ክፋ​ትን ወደ ጠላ​ቶች ይመ​ል​ሳ​ታል፤ በእ​ው​ነ​ት​ህም አጥ​ፋ​ቸው።


እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና።


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕን​ጨ​ትን አሳ​የው፤ በው​ኃ​ውም ላይ ጣለው፤ ውኃ​ውም ጣፈጠ። በዚ​ያም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ፈተ​ና​ቸው።


አቤቱ፥ በመ​ከ​ራዬ ጊዜ አሰ​ብ​ኹህ፤ በጥ​ቂት መከ​ራም ገሠ​ጽ​ኸኝ።


ለዳ​ዊት ቤትም፥ “አራም ከኤ​ፍ​ሬም ጋር ተባ​ብ​ረ​ዋል” የሚል ወሬ ተነ​ገረ፤ የእ​ር​ሱም ልብ የሕ​ዝ​ቡም ልብ የዱር ዛፍ በነ​ፋስ እን​ደ​ሚ​ና​ወጥ ተና​ወጠ።


አንቺ በሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በዝ​ግባ ዛፍም ውስጥ የም​ታ​ለ​ቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያ​ዘሽ ጊዜ እን​ዴት ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ!


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በም​ድረ በዳ ምን ያህል እን​ዳ​ሳ​ዘ​ን​ኸው፥ ከግ​ብፅ ሀገር ከወ​ጣ​ህ​በት ቀን ጀምሮ ወደ​ዚህ ስፍራ እስከ መጣ​ችሁ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፃ​ችሁ አስብ፤ አት​ር​ሳም።


ከዚ​ያም በኋላ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ወደ ባሕ​ሩም ገባ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች እስከ ኤር​ትራ ባሕር ድረስ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጮ​ሃ​ችሁ ጊዜ በእ​ና​ን​ተና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን መካ​ከል ደመ​ና​ንና ጭጋ​ግን አደ​ረ​ግሁ፤ ባሕ​ሩ​ንም መለ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ አሰ​ጠ​ማ​ቸ​ውም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በግ​ብፅ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን አዩ፤ በም​ድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።


ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።


跟着我们:

广告


广告