Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፈር​ዖን ሕዝ​ቡን በለ​ቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር መን​ገድ አል​መ​ራ​ቸ​ውም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ሕዝቡ ሰል​ፉን በአየ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ጸ​ጽ​ተው፥ ወደ ግብ​ፅም እን​ዳ​ይ​መ​ለስ” ብሎ​አ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ አቋራጭ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር በፍልስጥኤም ምድር በሚያልፈው መንገድ አልመራቸውም፤ “ጦርነት ቢያጋጥማቸው ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ ይመለሱ ይሆናል” ብሏልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ምንም እንኳን ቅርብ ቢሆን በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፦ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብጽም እንዳይመለስ” ብሏልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ቅርብ በሆነው በፍልስጥኤም የባሕር ጠረፍ በኩል ባለው መንገድ አልመራቸውም፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕዝቡ ከፊት ለፊታቸው ጦርነት እንደሚጠብቃቸው በሚያዩበት ጊዜ ሐሳባቸውን ለውጠው ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እንዲህም ሆነ፤ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፥ “ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው ወደ ግብፅም እንዳይመለስ” ብሎአልና።

参见章节 复制




ዘፀአት 13:17
14 交叉引用  

በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሆነው በል​ባ​ቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሳሉ ተመ​ል​ሰው፦ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል፥ በድ​ለ​ን​ማል፥ ክፉ​ንም አድ​ር​ገ​ናል ብለው ቢለ​ም​ኑህ፥


ለመ​ስ​ማ​ትም እንቢ አሉ፤ ያደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አላ​ሰ​ቡም፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ለባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም ወደ ግብፅ ይመ​ለሱ ዘንድ አለ​ቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓ​ሪና ይቅር ባይ አም​ላክ፥ ለቍ​ጣም የም​ት​ዘ​ገይ፥ ምሕ​ረ​ት​ንም የም​ታ​በዛ ነህ፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም።


ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።


ጳው​ሎስ ግን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሊወ​ስ​ደው አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እነ​ርሱ በጵ​ን​ፍ​ልያ ሳሉ ትቶ​አ​ቸው ሄዶ​አ​ልና፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ለሥራ አል​መ​ጣም ነበ​ርና።


አባ​ቶ​ቻ​ችን ለእ​ርሱ መታ​ዘ​ዝን እንቢ አሉ፤ ከዱ​ትም፤ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ ግብፅ ሀገር መለሱ።


ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።


ጸሐ​ፍ​ቱም ደግሞ ጨም​ረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድን​ጉጥ ሰው ቢሆን የወ​ን​ድ​ሞ​ቹን ልብ እንደ እርሱ እን​ዳ​ያ​ስ​ፈራ ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ ብለው ለሕ​ዝቡ ይና​ገሩ።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተመ​ል​ሰህ አታ​ያ​ትም ባል​ሁህ መን​ገ​ድም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ር​ከብ ወደ ግብፅ ይመ​ል​ስ​ሃል፤ በዚ​ያም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ የሚ​ራ​ራ​ላ​ች​ሁም አይ​ኖ​ርም።”


የን​ጉ​ሡ​ንም ቍጣ ሳይ​ፈራ፥ የግ​ብ​ፅን ሀገር በእ​ም​ነት ተወ፤ ከሚ​ያ​የው ይልቅ የማ​ይ​ታ​የ​ውን ሊፈራ ወዶ​አ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሁን እን​ግ​ዲህ፥ “የፈራ፥ የደ​ነ​ገ​ጠም ከገ​ለ​ዓድ ተራራ ተነ​ሥቶ ይመ​ለስ ብለህ በሕ​ዝቡ ጆሮ አውጅ” አለው። ከሕ​ዝ​ቡም ሃያ ሁለት ሺህ ተመ​ለሱ፤ ዐሥ​ርም ሺህ ቀሩ።


跟着我们:

广告


广告