Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ይህም ቀን መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ና​ችሁ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዓል ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ሥር​ዐት ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ር​ጉ​ታ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ይህን ቀን መታሰቢያ ታደርጉታላችሁ፤ በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ሆኖ የእግዚአብሔር በዓል አድርጋችሁ አክብሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔ እግዚአብሔር ያደረግኹላችሁን ሁሉ በማስታወስ ይህ ቀን መንፈሳዊ ክብረ በዓል ይሁንላችሁ፤ እርሱንም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ እንድታከብሩት ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፤ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 12:14
29 交叉引用  

ንጉ​ሡም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “በዚህ በቃል ኪዳኑ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን አድ​ርጉ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ለቅ​ኖች ብር​ሃን በጨ​ለማ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፤ አም​ላ​ካ​ች​ንም ጻድቅ ነው።


የኤ​ር​ት​ራን ባሕር ፈጽሞ የከ​ፈለ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


በዚ​ህም ቀን ሠራ​ዊ​ታ​ች​ሁን ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ዋ​ለ​ሁና ይህን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቁት፤ እን​ግ​ዲህ ይህን ቀን ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ።


ለእ​ና​ንተ ለል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሆ​ና​ችሁ ዘንድ ይህን ሕግ ጠብቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


የቂ​ጣ​ውን በዓል ጠብቁ፤ በአ​ዲስ ወር ከግ​ብፅ ምድር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚህ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”


ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ህ​ልን ቍር​ባን፥ በኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ስድ​ስ​ተኛ እጅ የስ​ንዴ ዱቄ​ትን፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ይህ የሚ​ደ​ረግ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ሥር​ዐት ነው።


በዚ​ህም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቂጣ በዓል ነው፤ ሰባት ቀን ቂጣ ብሉ።


አክሊሎችም ለሔሌምና ለጦብያ ለዮዳኤም ለሶፎንያስም ልጅ ለሔን በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ ለመታሰቢያ ይሆናሉ።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ካህ​ናቱ መለ​ከ​ቱን ይንፉ፤ ይህም ለልጅ ልጃ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁ​ን​ላ​ችሁ።


ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ የለ​ዩ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ቍር​ባ​ኔን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ንተ እስ​ክ​ታ​ረጅ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።”


ኅብ​ስ​ቱ​ንም አነሣ፤ አመ​ስ​ገነ፤ ፈት​ቶም ሰጣ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ስለ እና​ንተ ቤዛ ሆኖ የሚ​ሰጥ ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህ​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢ​ያዬ አድ​ር​ጉት፤”


“በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ሀገር በሌ​ሊት ወጥ​ተ​ሃ​ልና የሚ​ያ​ዝ​ያን ወር ጠብ​ቀህ፥ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ አድ​ርግ።


አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ህም ያሉ መጻ​ተ​ኛና ድሃ-አደግ፥ መበ​ለ​ትም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ በሚ​መ​ር​ጠው ስፍራ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


በእ​ጅ​ህም እንደ ምል​ክት አድ​ር​ገው፤ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁ​ን​ልህ።


አንተ በም​ድር ሁሉ ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስን​ሻ​ገር የዮ​ር​ዳ​ኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነ​ዚህ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ናሉ።”


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ትና ሕግ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告