Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ወገ​ቦ​ቻ​ች​ሁን ታጥ​ቃ​ችሁ፥ ጫማ​ች​ሁን በእ​ግ​ራ​ችሁ ተጫ​ም​ታ​ችሁ፥ በት​ራ​ች​ሁ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ይዛ​ችሁ እን​ዲህ ብሉት፦ እየ​ቸ​ኰ​ላ​ች​ሁም ትበ​ሉ​ታ​ላ​ችሁ፤ እርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነውና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ስትበሉም ልብሳችሁን ለብሳችሁ፣ በዐጭር ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አድርጋችሁ በትራችሁን ይዛችሁ በጥድፊያ ብሉት፤ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንግዲህ ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ብሉት፤ ለጌታ ፋሲካ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ለጒዞ እንደ ተዘጋጀ ሰው ሆናችሁ ወገባችሁን በመታጠቅ ጫማችሁን አድርጋችሁ፥ በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ በችኰላ ብሉት፤ እርሱም እኔን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት የፋሲካ በዓል ይሁንላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችህ፤

参见章节 复制




ዘፀአት 12:11
21 交叉引用  

ንጉ​ሡም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “በዚህ በቃል ኪዳኑ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲ​ካን አድ​ርጉ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ደሙም ባላ​ች​ሁ​ባ​ቸው ቤቶች ምል​ክት ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል፤ ደሙ​ንም አያ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እሰ​ው​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም የግ​ብ​ፅን ሀገር በመ​ታሁ ጊዜ የጥ​ፋት መቅ​ሠ​ፍት አይ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ አላ​ቸው፥ “ሂዱና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ ጠቦት ውሰዱ፤ ለፋ​ሲ​ካም እረ​ዱት።


‘ይህ በግ​ብፅ ሀገር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንን የአ​ዳነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት ነው’ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሕዝ​ቡም ተጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን አላ​ቸው፥ “ይህ የፋ​ሲካ ሕግ ነው፤ ከእ​ርሱ ባዕድ ሰው አይ​ብላ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካን በዓል ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እስከ ሰባት ቀንም ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሲመሽ የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በሲና ምድረ በዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


“ወገ​ባ​ችሁ የታ​ጠቀ መብ​ራ​ታ​ች​ሁም የበራ ይሁን።


አባ​ቱም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ‘ያማሩ ልብ​ሶ​ችን ቶሎ አም​ጡና አል​ብ​ሱት፤ ለጣ​ቱም ቀለ​በት፥ ለእ​ግ​ሩም ጫማ አድ​ር​ጉ​ለት፤’


ዘመ​ዶ​ቹም በየ​ዓ​መቱ ለፋ​ሲካ በዓል ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሄዱ ነበር።


በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም በእ​ግ​ሮቹ አጠ​ገብ ቆማ አለ​ቀ​ሰች፤ እግ​ሮ​ቹ​ንም በእ​ን​ባዋ ታርስ ነበር፥ በራስ ጠጕ​ር​ዋም እግ​ሮ​ቹን ታብ​ሰ​ውና ትስ​መው፥ ሽቱም ትቀ​ባው ነበር።


እን​ግ​ዲህ ለአ​ዲስ ቡሆ ትሆኑ ዘንድ አሮ​ጌ​ውን እርሾ ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ ገና ቂጣ ናች​ሁና፤ ፋሲ​ካ​ችን ክር​ስ​ቶስ ተሠ​ውቶ የለ​ምን?


የሰ​ላም ወን​ጌል ኀይ​ል​ንም ተጫ​ም​ታ​ችሁ ቁሙ።


“በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ሀገር በሌ​ሊት ወጥ​ተ​ሃ​ልና የሚ​ያ​ዝ​ያን ወር ጠብ​ቀህ፥ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ አድ​ርግ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በጌ​ል​ገላ ሰፈሩ፤ ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን በመሸ ጊዜ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በኢ​ያ​ሪኮ ምዕ​ራብ ፋሲ​ካን አደ​ረጉ።


ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።


跟着我们:

广告


广告