Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሙሴም አለው፥ “እኛ ከታ​ና​ና​ሾ​ቻ​ች​ንና ከሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ችን፥ ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ቻ​ች​ን​ንና ላሞ​ቻ​ች​ን​ንም እን​ወ​ስ​ዳ​ለን። የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ነውና።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሙሴም፣ “ለእግዚአብሔር በዓል ልናከብር ስለ ሆነ ወጣቶቻችንንና ሽማግሌዎቻችንን፣ ወንድና ሴት ልጆቻችንን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻችንን እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻችንን ይዘን እንሄዳለን” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሙሴም “ሕፃን ልጆቻችንና ሽማግሌዎቻችን ሳይቀሩ ሁላችንም እንሄዳለን፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን፥ በጎቻችንንና ፍየሎቻችንን፥ የቀንድ ከብቶቻችንንም ሁሉ እንወስዳለን፤ በምንሄድበት ስፍራ ለእግዚአብሔር በዓል እናደርጋለን” ሲል መለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሙሴም፦ “እኛ እንሄዳለን፤ የእግዚአብሔርም በዓል ሆኖልናልና ታናናሾቻችንና ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም፥ በጎቻችንና ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፤” አለ።

参见章节 复制




ዘፀአት 10:9
19 交叉引用  

የዮ​ሴ​ፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የአ​ባ​ቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ብቻ በጌ​ሤም ተዉ።


ፈር​ዖ​ንም አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እና​ን​ተን ስለቅ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም መል​ቀቅ አለ​ብ​ኝን? ክፉ ነገር እን​ደ​ሚ​ገ​ጥ​ማ​ችሁ ዕወቁ።


ከብ​ቶ​ቻ​ችን ከእኛ ጋር ይሄ​ዳሉ፤ አንድ ሰኰ​ናም አይ​ቀ​ርም፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ም​ለክ ከእ​ነ​ርሱ እን​ወ​ስ​ዳ​ለ​ንና፤ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ደ​ም​ና​መ​ል​ከው ከዚያ እስ​ክ​ን​ደ​ርስ አና​ው​ቅም።”


በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ላሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ኩኝ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ።


ስድ​ስት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ሰባ​ተ​ኛ​ውም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል ይሆ​ናል።


እነ​ር​ሱም ቃል​ህን ይሰ​ማሉ፤ አን​ተና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገ​ባ​ላ​ችሁ፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠር​ቶ​ናል፤ አሁ​ንም ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠዋ ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን ትሉ​ታ​ላ​ችሁ።


ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”


እነ​ር​ሱም፥ “ቸነ​ፈር ወይም ሰይፍ እን​ዳ​ይ​ጥ​ል​ብን የሦ​ስት ቀን መን​ገድ በም​ድረ በዳ እን​ድ​ን​ሄድ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ድ​ን​ሠዋ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ ጠራን” አሉት።


እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።


የጭ​ን​ቀት ቀን ሳይ​መጣ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ወራት ፈጣ​ሪ​ህን ዐስብ፤ ደስ አያ​ሰ​ኙም የም​ት​ላ​ቸው ዓመ​ታት ሳይ​ደ​ርሱ፥


“በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ዐሥራ አም​ስ​ተ​ኛዋ ቀን ለእ​ና​ንተ የተ​ቀ​ደ​ሰች ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ የተ​ግ​ባ​ርን ሥራ ሁሉ አት​ሥ​ሩ​ባት፤ ሰባት ቀንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓል አድ​ርጉ።


እና​ን​ተም አባ​ቶች ሆይ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተግ​ሣ​ጽና ምክር አሳ​ድ​ጉ​አ​ቸው እንጂ አታ​ስ​ቈ​ጡ​አ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ልኩ ዘንድ ባት​ወ​ድዱ ግን፥ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በወ​ንዝ ማዶ ሳሉ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት፥ ወይም በም​ድ​ራ​ቸው ያላ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት ታመ​ልኩ እንደ ሆነ፥ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።”


跟着我们:

广告


广告