ዘፀአት 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እንዲህም አይደለም፤ እናንተ ወንዶቹ ሂዱ፤ ይህን ፈልጋችኋልና እግዚአብሔርን አምልኩ” አላቸው። ሙሴንና አሮንንም ከፈርዖን ፊት አስወጡአቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 አይሆንም፤ ወንዶቹ ብቻ እንዲሄዱና እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አድርጉ፤ የጠየቃችሁት ይህንኑ ነው።” ከዚያም ሙሴና አሮን ከፈርዖን ፊት እንዲወጡ ተደረገ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እንዲህ አይሆንም፤ እናንተ ወንዶቹ ሂዱና ጌታን አገልግሉ፥ የጠየቃችሁት ይህንን ነውና።” ከፈርዖንም ፊት አባረሩአቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እንግዲህ እግዚአብሔርን ማገልገል ከፈለጋችሁ ወንዶቹ ብቻ መሄድ ትችላላችሁ”። ከዚህም በኋላ ሙሴና አሮን ተባረው ወጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እንዲህም አይይደለም፤ እናንተ ወንዶቹ ሂዱ፤ ይህን ፈልጋችኋልና እግዚአብሔርን አገልግሉ፤” አላቸው። ከፈርዖንም ፊት አባረሩአቸው። 参见章节 |