Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እኔ የፈ​ር​ዖ​ን​ንና የሹ​ሞ​ቹን ልብ አጽ​ን​ቼ​አ​ለ​ሁና፥ ተአ​ም​ራቴ በእ​ነ​ርሱ ላይ በት​ክ​ክል ይመጣ ዘንድ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ተመልሰህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች በመካከላቸው ለማድረግ የፈርዖንንና የሹማምቱን ልብ አደንድኛለሁና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ ፈርዖን ግባ እኔ ልቡንና የአገልጋዮቹን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው ምልክቶቼን እንዳሳይ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እነሆ እንደገና ወደ ፈርዖን ተመልሰህ ግባ፤ እኔ የእርሱንና የመኳንንቱን ልብ ያደነደንኩት በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ ዐቅጄ ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ የእርሱንና የባሪያዎቹን ልብ አደንድኛለሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 10:1
19 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ው​ነት ዳኛ ነው፤ ኀይ​ለ​ኛም ታጋ​ሽም ነው፤ ሁል​ጊ​ዜም ጥፋ​ትን አያ​መ​ጣም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አል​ል​ቀ​ቀም።


እኔም እጄን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በማ​ደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ውም ተአ​ም​ራቴ ሁሉ ግብ​ፅን እመ​ታ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይለ​ቅ​ቋ​ች​ኋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


ፈር​ዖ​ንም አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጄ​ንም በግ​ብፅ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሕዝ​ቤን በኀ​ይሌ በታ​ላቅ ፍርድ ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙ​ሴና ለአ​ሮን እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ነገር ግን ኀይ​ሌን እገ​ል​ጥ​ብህ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ላይ ይነ​ገር ዘንድ ስለ​ዚህ ጠበ​ቅ​ሁህ።


ፈር​ዖ​ንም ልኮ ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠራ፤ “አሁ​ንም በደ​ልሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢ​አ​ተ​ኞች ነን።


“በዐ​ይ​ና​ቸው አይ​ተው፥ በል​ባ​ቸ​ውም አስ​ተ​ው​ለው እን​ዳ​ይ​መ​ለ​ሱና እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው ታወሩ፤ ልባ​ቸ​ውም ደነ​ደነ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለፈ​ር​ዖን በመ​ጽ​ሐፍ እን​ዲህ አለው፥ “ኀይ​ሌን በአ​ንተ ላይ እገ​ልጥ ዘንድ፥ ስሜም በም​ድር ሁሉ ይሰማ ዘንድ ስለ​ዚህ አስ​ነ​ሣ​ሁህ።”


እነሆ፥ የሚ​ወ​ድ​ደ​ውን ይም​ረ​ዋል፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ልቡን ያጸ​ና​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ፥ ያጠ​ፉ​አ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ይ​ራ​ሩ​ላ​ቸው ፈጽ​መው እን​ዲ​ያ​ጠ​ፉ​አ​ቸው፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይጋ​ጠሙ ዘንድ ልባ​ቸ​ውን እን​ዲ​ያ​ደ​ነ​ድኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልባ​ቸ​ውን አጸና።


ወዮ​ልን! ከእ​ነ​ዚህ ኀያ​ላን አማ​ል​ክት እጅ ማን ያድ​ነ​ናል? እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በም​ድረ በዳ በልዩ ልዩ መቅ​ሠ​ፍት የመቱ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告