Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤፌሶን 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በከ​ንቱ ነገ​ርም የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ አይ​ኑር፤ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት በከ​ሓ​ዲ​ዎች ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓት ይመ​ጣ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ የሚመጣው በእንደዚህ ዐይነት ነገር ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በእነዚህ ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ሰዎች ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ስለሚመጣ ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከዚህ የተነሣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣልና ማንም በከንቱ ንግግር አያታልላችሁ።

参见章节 复制




ኤፌሶን 5:6
28 交叉引用  

የከ​ን​ፈር ቃል ለሰ​ልፍ ምክ​ርና ኀይል እን​ደ​ሚ​ሆን ትና​ገ​ራ​ለህ፤ አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው?


እና​ንተ ግን፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕልም ዐላ​ሚ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ባለ ራእ​ዮ​ቻ​ች​ሁን፥ መተ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም አት​ስሙ፤


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አይ​ሄ​ዱ​ምና፦ ከለ​ዳ​ው​ያን በር​ግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄ​ዳሉ ብላ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን አታ​ታ​ልሉ።


እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።


ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ያስቱ ዘንድ ምልክትና ድንቅ ያደርጋሉ።


ኢየሱስም መልሶ እንዲህ ይላቸው ጀመር “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።


እው​ነ​ትን ዐው​ቀው በክ​ፋ​ታ​ቸው በሚ​ለ​ው​ጡ​አት በዐ​መ​ፀ​ና​ውና በኀ​ጢ​አ​ተ​ናው ሰው ሁሉ ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት ከሰ​ማይ ይመ​ጣል።


በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።


ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው።


ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ።


በእ​ነ​ር​ሱም ምክ​ን​ያት በማ​ይ​ታ​ዘዙ ልጆች ላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ጣል።


ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዐመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና።


ሌላ ልዩ ትም​ህ​ርት አታ​ምጡ፤ ልባ​ችሁ በመ​ብል ያይ​ደለ በጸጋ ቢጸና ይበ​ል​ጣ​ልና፤ በዚያ ይሄዱ የነ​በሩ እነ​ዚያ አል​ተ​ጠ​ቀ​ሙ​ምና።


አላ​መ​ኑ​ምና፥ ለመ​ግ​ባት እን​ዳ​ል​ቻሉ እነሆ፥ እና​ያ​ለን።


የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤” የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።


ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።


跟着我们:

广告


广告