ኤፌሶን 5:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ከቶ ሥጋውን መጥላት የሚቻለው የለም፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ መገባት መግቡ፤ ጠብቁም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም29 የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ማንም የለም፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋል፤ ክርስቶስም ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው ልክ እንደዚሁ ነው፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ማንም የራሱን እካል የሚጠላ ከቶ የለምና፤ ይመግበዋል፤ ይንከባከበውማል። ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው እንዲህ ነው፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 የገዛ ራሱን አካል የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቅስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን እንደሚያደርገው ዐይነት ራሱን ይመግባል፤ ይንከባከባልም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29-30 ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና፥ ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን፥ ክርስቶስ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን እንዳደረገላት፥ ይመግበዋል ይከባከበውማል። 参见章节 |