Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤፌሶን 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት ለባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ለክርስቶስ ካላችሁ አክብሮታዊ ፍርሀት የተነሣ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ተገዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ለክርስቶስ ክብር ብላችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ለሌላው ይታዘዝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ።

参见章节 复制




ኤፌሶን 5:21
20 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም፥ “ወደ እመ​ቤ​ትሽ ተመ​ለሺ፤ ከእ​ጅ​ዋም በታች ራስ​ሽን ዝቅ አድ​ርጊ” አላት።


አለ​ቆ​ቹም ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑም፥ ደግ​ሞም የን​ጉሡ የአ​ባቱ የዳ​ዊት ልጆች ሁሉ ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን ተገ​ዙ​ለት።


አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


ደግ​ሞም አልሁ፥ “የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሕ​ዛብ እን​ዳ​ይ​ሰ​ድ​ቡን አም​ላ​ካ​ች​ንን በመ​ፍ​ራት ትሄዱ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ች​ሁ​ምን?


ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ ከእነርሱ ለአንዱ ስንኳ እንቢ አትበል።


እና​ን​ተም እንደ እነ​ዚህ ላሉ​ትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባ​ብሮ ለሚ​ደ​ክም ሁሉ ትታ​ዘ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ዐው​ቀን ሰዎ​ችን እና​ሳ​ም​ና​ለን፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እኛ የተ​ገ​ለ​ጥን ነን፤ እን​ዲ​ሁም በል​ቡ​ና​ችሁ የተ​ገ​ለ​ጥን እንደ ሆን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ግ​ዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለ​ሆን ራሳ​ች​ንን እና​ንጻ፤ ሥጋ​ች​ንን አና​ር​ክስ፤ ነፍ​ሳ​ች​ን​ንም አና​ሳ​ድፍ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት የም​ን​ቀ​ደ​ስ​በ​ትን እን​ሥራ።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ።


ሴቶ​ችም ለጌ​ታ​ችን እን​ደ​ሚ​ታ​ዘዙ ለባ​ሎ​ቻ​ቸው ይታ​ዘዙ።


ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ለክ​ር​ስ​ቶስ እን​ደ​ም​ት​ታ​ዘዝ፥ እን​ዲ​ሁም ሴቶች ለባ​ሎ​ቻ​ቸው በሁሉ ይታ​ዘዙ።


በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ።


ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤


ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤


ለመ​ም​ህ​ሮ​ቻ​ችሁ ታዘዙ፤ ተገ​ዙ​ላ​ቸ​ውም፤ ስለ እና​ንተ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምላሽ የሚ​ሰጡ እንደ መሆ​ና​ቸው፥ ይህን ሳያ​ዝኑ ደስ ብሎ​አ​ቸው ያደ​ር​ጉት ዘንድ ስለ ነፍ​ሳ​ችሁ ይተ​ጋ​ሉና።


ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዐት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤


ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።


跟着我们:

广告


广告