Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤፌሶን 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ርጎ አስ​ገ​ዛ​ለት፤ ከሁሉ በላይ የሆነ እር​ሱን ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ አደ​ረ​ገው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔርም ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም በማንኛውም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሁሉንም ነገር በሥልጣኑ ሥር አድርጎ አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም ከሁሉ በላይ እንዲሆን ራስ አደረገው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።

参见章节 复制




ኤፌሶን 1:22
18 交叉引用  

በአ​ን​ተና በሴ​ቲቱ መካ​ከል፥ በዘ​ር​ህና በዘ​ር​ዋም መካ​ከል ጠላ​ት​ነ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እርሱ ራስ​ህን ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፤ አን​ተም ሰኰ​ና​ውን ትነ​ድ​ፋ​ለህ።”


አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የተ​ተ​ከሉ ናቸው፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አደ​ባ​ባይ ውስጥ ይበ​ቅ​ላሉ።


እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


ነገር ግን የወ​ንድ ሁሉ ራሱ ክር​ስ​ቶስ፥ የሴ​ትም ራስዋ ወንድ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ራሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


ለእ​ርሱ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ፥ በት​ው​ልድ ሁሉ ምስ​ጋና ይሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አሜን።


ክር​ስ​ቶስ አካሉ ለሆ​ነ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስዋ አዳ​ኝ​ዋም እንደ ሆነ ወንድ ለሴት ራስዋ ነውና።


እርሱ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ ነው፤ በኵር እርሱ ለሁሉ ራስ ይሆን ዘንድ ከሙ​ታን ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና።


እር​ሱም በመ​ን​ፈስ መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁን ነገ​ረን።


እና​ን​ተም በእ​ርሱ ፍጹ​ማን ሁኑ፤ እርሱ ለአ​ለ​ቅ​ነት ሁሉና ለሥ​ል​ጣን ሁሉ ራስ ነውና።


ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚ​ኖ​ር​በት፥ በሥ​ርና በጅ​ማ​ትም በሚ​ስ​ማ​ማ​በት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ያ​ድ​ግ​በ​ትና በሚ​ጸ​ና​በት፥ በሚ​ሞ​ላ​በ​ትም በራስ አይ​ጸ​ናም።


ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።


ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ር​ገህ አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት።” ሁሉን ለእ​ርሱ ባስ​ገ​ዛ​ለት ጊዜም የተ​ወ​ውና ያላ​ስ​ገ​ዛ​ለት የለም፤ አሁን ግን ሁሉን እን​ዳ​ስ​ገ​ዛ​ለት አና​ይም።


跟着我们:

广告


广告