Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 8:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከፀ​ሓ​ይም በታች የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሥራ መር​ምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እን​ዳ​ይ​ቻ​ለው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈ​ልግ እጅግ ቢደ​ክም መር​ምሮ አያ​ገ​ኘ​ውም፤ ደግ​ሞም ጠቢብ ሰው፥ “ይህን ዐወ​ቅሁ” ቢል እርሱ ያገ​ኘው ዘንድ አይ​ች​ልም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አምላክ ያደረገውን ሁሉ አየሁ። ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ሰው ለመመርመር ብዙ ቢጥርም፣ ትርጕሙን ማግኘት አይችልም፤ ጠቢብም እንኳ ዐውቀዋለሁ ቢል፣ ፈጽሞ ሊገነዘበው አይችልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የእግዚአብሔርንም ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እርሱም ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ሰው ማግኘት አለመቻሉን፥ ሰውም በመፈለግ እጅግ ቢደክምም መርምሮ አለማግኘቱን ነው፥ ደግሞም ጠቢብ ሰው አውቀዋለሁ ቢልም እንኳን ይህንን ለማግኘት አይችልም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሰው በምርምር ብዛትም እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ማወቅ እንደማይችል አረጋገጥኩ፤ ሰው ብዙ ነገር መርምሮ ለማወቅ የቱንም ያኽል ቢደክም አንዳች ነገር ማግኘት አይችልም፤ በእርግጥ ጥበበኞች ሰዎች “ይህንን እናውቃለን” ለማለት ይደፍሩ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የሚያውቁት ነገር የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከፀሐይም በታች የተደረገውን ሥራ መርምሮ ያገኝ ዘንድ ለሰው እንዳይቻለው የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ አየሁ። ሰውም ሊፈልግ እጅግ ቢደክም መርምሮ አያገኘውም፥ ደግሞ ጠቢብ ሰው፦ ይህን አወቅሁ ቢል እርሱ ያገኘው ዘንድ አይችልም።

参见章节 复制




መክብብ 8:17
13 交叉引用  

እርሱ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ታላቅ ነገ​ርና የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ውን የከ​በ​ረና ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።


ሕዝ​ቡ​ንም እጅግ አበ​ዛ​ቸው፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ይልቅ አበ​ረ​ታ​ቸው።


ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦ “መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።


ቀኑ የአ​ንተ ነው፥ ሌሊ​ቱም የአ​ንተ ነው፤ አንተ ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን ፈጠ​ርህ።


ከሰ​ማ​ይም በታች ስለ​ተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በጥ​በብ ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ፈ​ተን ልቤን አተ​ጋሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ ክፉ ድካ​ምን ለሰው ልጆች ሰጥ​ት​ዋ​ልና።


የነ​ፋስ መን​ገድ እን​ዴት እንደ ሆነች፥ አጥ​ን​ትም በእ​ር​ጉዝ ሆድ እን​ዴት እን​ድትዋ​ደድ እን​ደ​ማ​ታ​ውቅ፥ እን​ዲ​ሁም ሁሉን የሚ​ሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አታ​ው​ቅም።


የሠ​ራው ሥራ ሁሉ በጊ​ዜው መል​ካም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠ​ራ​ውን ሥራ ሰው መር​ምሮ እን​ዳ​ያ​ገኝ ዘለ​ዓ​ለ​ም​ነ​ትን በልቡ ሰጠው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ተመ​ል​ከት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠማማ ያደ​ረ​ገ​ውን ማን ሊያ​ቀ​ናው ይች​ላል?


አሁ​ንም አላ​ወ​ቅ​ህ​ምን? አል​ሰ​ማ​ህ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አም​ላክ፥ የም​ድ​ር​ንም ዳርቻ የፈ​ጠረ አም​ላክ ነው፤ አይ​ራ​ብም፤ አይ​ጠ​ማም፤ አይ​ደ​ክ​ምም፤ ማስ​ተ​ዋ​ሉም አይ​መ​ረ​መ​ርም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም።


跟着我们:

广告


广告