Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከፀ​ሓይ በታች በም​ድር የሚ​ደ​ረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃ​ጥ​ኣን የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸው ጻድ​ቃን አሉ፥ ለጻ​ድ​ቃ​ንም የሚ​ደ​ረ​ገው ሥራ የሚ​ደ​ር​ስ​ላ​ቸው ኃጥ​ኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በምድር ላይ የሚከሠት ሌላም ከንቱ ነገር አለ፤ ጻድቃን ለክፉዎች የሚገባውን፣ ክፉ ሰዎችም ለጻድቃን የሚገባውን ይቀበላሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ነው አልሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በክፉዎች ላይ የሚደረገው የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው የሚደርስላቸው ክፉዎችም አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በምድር ላይ የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፤ አንዳንድ ጊዜ ደጋግ ሰዎች ለክፉ ሰዎች የሚገባውን ቅጣት ይቀበላሉ፤ ክፉ ሰዎች ደግሞ ለደጋግ ሰዎች የሚገባውን ዋጋ ያገኛሉ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ነው አልኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኀጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኀጥኣን አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።

参见章节 复制




መክብብ 8:14
16 交叉引用  

በዚ​ህም በደ​ረ​ሰ​በት ሁሉ ኢዮብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አል​በ​ደ​ለም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስን​ፍ​ናን አል​ሰ​ጠም።


ስለ ምን ኀጢ​ኣ​ተ​ኞች በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራሉ? በባ​ለ​ጠ​ግ​ነ​ትስ ስለ ምን ያረ​ጃሉ?


እነሆ፥ ሁላ​ች​ሁም፥ በክ​ፉ​ዎች ላይ ክፋት እን​ደ​ም​ት​መ​ጣ​ባ​ቸው ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ጠላት በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁል​ጊዜ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ላይ እጅ​ህን አንሣ።


ከፀ​ሓይ በታች ያየ​ሁት ክፉ ነገር አለ፥ እር​ሱም ከገዢ ባለ​ማ​ወቅ የሚ​ወጣ ስሕ​ተት ነው፥


የጠ​ቢብ ዐይ​ኖች በራሱ ላይ ናቸ​ውና፤ አላ​ዋቂ ግን በጨ​ለማ ይሄ​ዳል፤ ደግሞ የሁ​ለ​ቱም መጨ​ረ​ሻ​ቸው አንድ እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።


እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።


ጻድቅ በጽ​ድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥ​እም በክ​ፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከ​ንቱ ዘመኔ አየሁ።


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፣ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።


跟着我们:

广告


广告