Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እን​ዲ​ሁም ያን​ጊዜ ኃጥ​ኣን ወደ ጽኑ መቃ​ብር ሲገቡ አየሁ፥ ከቅ​ድ​ስት ስፍ​ራም ወጥ​ተው ተለዩ፤ እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማዋ ተመ​ሰ​ገኑ፥ እን​ዲህ ሠር​ተ​ዋ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲሁም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይመጡና ይሄዱ የነበሩት ክፉዎች ተቀብረው አየሁ፤ ይህን ባደረጉበት ከተማም ይመሰገኑ ነበር፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንዲሁም ክፉዎች ተቀብረው አየሁ፥ ነገር ግን ቅን አድራጊዎች ከቅድስት ስፍራ ወጡ፥ በከተማይቱም ውስጥ ተረሱ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ክፉዎች በክብር ሲቀበሩ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ሰዎች ግን ከቅድስቲቱ ከተማ ወጥተው በመሄድ ተረሱ፤ ይህ ሁሉ ከንቱ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንዲሁም ኀጥኣን ተቀብረው አየሁ፥ ወደ ዕረፍትም ገቡ፥ ነገር ግን ቅን አድራጊዎች ከቅድስት ስፍራ ወጡ፥ በከተማይቱም ውስጥ ተረሱ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

参见章节 复制




መክብብ 8:10
14 交叉引用  

በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


ለፊ​ተ​ኞቹ ነገ​ሮች መታ​ሰ​ቢያ የላ​ቸ​ውም፤ ለኋ​ለ​ኞ​ቹም ነገ​ሮች ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በሚ​ነ​ሡት ሰዎች ዘንድ መታ​ሰ​ቢያ አይ​ገ​ኝ​ላ​ቸ​ውም።


ለብ​ልህ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የለ​ውም፤ እነሆ፥ ዘመን ይመ​ጣ​ልና ሁሉም ይረ​ሳል፤ ብል​ህስ ከአ​ላ​ዋቂ ጋር እን​ዴት ይሞ​ታል?


ጠቢብ ድሃ ሰውም በው​ስ​ጥዋ ተገ​ኘ​ባት፥ ያች​ንም ከተማ በጥ​በቡ አዳ​ናት፤ ያን ድሃ ሰው ግን ማንም አላ​ሰ​በ​ውም።


ሕያ​ዋን እን​ዲ​ሞቱ ያው​ቃ​ሉና፤ ሙታን ግን አን​ዳች አያ​ው​ቁም፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውም ተረ​ስ​ቶ​አ​ልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላ​ቸ​ውም።


አቤቱ! የእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ ሆይ! የሚ​ተ​ዉህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ለዩ የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ ምንጭ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተ​ዋ​ልና በም​ድር ላይ ይጻ​ፋሉ።


ከዚ​ህም በኋላ ድሃው ሞተ፤ መላ​እ​ክ​ትም ወደ አብ​ር​ሃም አጠ​ገብ ወሰ​ዱት፤ ባለ​ጸ​ጋ​ውም ደግሞ ሞተ፤ ተቀ​በ​ረም፤


የሐ​ሰት ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ሙ​በት፤ እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅ​ደስ ላይና በኦ​ሪት ላይ የስ​ድብ ቃል እየ​ተ​ና​ገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤


ጻድቅ በእ​ም​ነት ይድ​ናል፤ ወደ​ኋላ ቢመ​ለስ ግን ልቡ​ናዬ በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ትም።”


跟着我们:

广告


广告