Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በም​ት​ሄ​ድ​በት ጊዜ እግ​ር​ህን ጠብቅ፤ የጠ​ቢ​ባ​ን​ንም ትም​ህ​ርት ለመ​ስ​ማት ቅረብ፤ ዳግ​መ​ኛም ከሰ​ነ​ፎች ስጦታ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ከመ​ቀ​በል ተጠ​በቅ፤ እነ​ርሱ መል​ካም ለመ​ሥ​ራት ዐዋ​ቂ​ዎች አይ​ደ​ሉ​ምና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሞኞችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትቸኩል፥ ልብህም በእግዚአብሔር ፊት ቃልን ለመናገር አይቸኩል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትገባበት ጊዜ ለአረማመድህ ጥንቃቄ አድርግ፤ እዚያ ሄዶ ደጉን ከክፉ ለይተው የማያውቁ ሞኞች ሰዎች እንደሚያደርጉት መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ የምክር ቃላትን ለመስማት ዝግጁ ሆኖ መገኘት ይበልጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፥ ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዋዕት ይበልጣልና፥ እነርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና።

参见章节 复制




መክብብ 5:1
28 交叉引用  

ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ።


“ብዙ እን​ደ​ም​ት​ና​ገር እን​ዲሁ መስ​ማት አለ​ብህ። ወይስ በን​ግ​ግ​ርህ ብዛት ጻድቅ የም​ት​ሆን ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? ከሴ​ቶች የሚ​ወ​ለድ ዘመኑ ጥቂት የሆነ ቡሩክ ነው።


“ልዑል የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ የሚ​ገ​ባው አይ​ደ​ለ​ምን? ትዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንስ አያ​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ው​ምን?


እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።


“ወደ​ዚህ አት​ቅ​ረብ፤ አንተ የቆ​ም​ህ​ባት ስፍራ የተ​ቀ​ደ​ሰች መሬት ናትና፥ ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አውጣ” አለው።


“የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰን ከናስ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ከናስ ሥራ፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ውኃም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ።


ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።


በሬን የሚ​ሠ​ዋ​ልኝ ኃጥእ ውሻን እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ድ​ልኝ ነው፤ የእ​ህ​ልን ቍር​ባን የሚ​ያ​ቀ​ር​ብም የእ​ሪ​ያን ደም እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ ነው፤ ዕጣ​ን​ንም ለመ​ታ​ሰ​ቢያ የሚ​ያ​ጥን አም​ላ​ክን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እነ​ዚህ የገዛ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን መረጡ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው ደስ ይላ​ታል።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ እኔ በሚ​ቀ​ርቡ እመ​ሰ​ገ​ና​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ፊት እከ​ብ​ራ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው” አለው፤ አሮ​ንም ደነ​ገጠ።


ስለ​ዚ​ህም ወዲ​ያ​ውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመ​ም​ጣ​ት​ህም መል​ካም አደ​ረ​ግህ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ሁሉ ልን​ሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ አለን።”


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።


በውኑ የም​ት​በ​ሉ​በ​ትና የም​ት​ጠ​ጡ​በት ቤት የላ​ች​ሁ​ምን? ወይስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ታስ​ነ​ቅ​ፋ​ላ​ች​ሁን? ነዳ​ያ​ን​ንስ ታሳ​ፍ​ሩ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ች​ሁን? ምን እላ​ለሁ? በዚህ አመ​ሰ​ግ​ና​ች​ኋ​ለ​ሁን? አላ​መ​ሰ​ግ​ና​ች​ሁም።


እው​ነ​ትን ካወ​ቅ​ናት በኋላ፥ ተጋ​ፍ​ተን ብን​በ​ድል ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አይ​ኖ​ርም።


ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ኢያ​ሱን፥ “አንተ የቆ​ም​ህ​በት ስፍራ የተ​ቀ​ደሰ ነውና ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አው​ልቅ” አለው። ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረገ።


跟着我们:

广告


广告