Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ ብቸኛ ሰው አለ፤ ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤ እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው? ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዓይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው።

参见章节 复制




መክብብ 4:8
21 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “ሰው ብቻ​ውን ይኖር ዘንድ መል​ካም አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ረ​ዳ​ውን ጓደኛ እን​ፍ​ጠ​ር​ለት እንጂ።”


መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ቍር​ባ​ንን አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ ሥጋ​ህን አን​ጻ​ልኝ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና ስለ ኀጢ​አት የሚ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አል​ወ​ደ​ድ​ሁም።


በዚ​ያን ጊዜ አልሁ፥ “እነሆ፥ መጣሁ፤ ስለ እኔ በመ​ጽ​ሐፍ ራስ ተጽ​ፎ​አል፤


ከሰ​ማ​ይም በታች ስለ​ተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በጥ​በብ ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ፈ​ተን ልቤን አተ​ጋሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ ክፉ ድካ​ምን ለሰው ልጆች ሰጥ​ት​ዋ​ልና።


ነገር ሁሉ ያደ​ክ​ማል፤ ሰውም ይና​ገ​ረው ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ዐይን በማ​የት አይ​ጠ​ግ​ብም፥ ጆሮም በመ​ስ​ማት አይ​ሞ​ላም።


ሰው በጥ​በ​ብና በዕ​ው​ቀት በብ​ር​ታ​ትም ከደ​ከመ በኋላ ለሌላ ላል​ደ​ከ​መ​በት ሰው ዕድ​ሉን ያወ​ር​ሳ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትል​ቅም መከራ ነው።


ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚ​ያም ነው፤ ልቡም በሌ​ሊት አይ​ተ​ኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ከንቱ ነገ​ርን አየሁ።


ብርን የሚ​ወ​ድድ ሰው ብርን አይ​ጠ​ግ​ብም፤ ብዙ እህ​ል​ንም የሚ​ወ​ድድ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው።


የም​ድር ጥቅም ለሁሉ ነው፥ የን​ጉ​ሥም ጥቅም በእ​ርሻ ነው።


ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ቸው እርሻ ይወ​ስዱ ዘንድ፥ ምድ​ር​ንም ለብ​ቻ​ቸው ይይ​ዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚ​ያ​ያ​ይዙ፥ እር​ሻ​ንም ከእ​ርሻ ጋር ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ርቡ ወዮ​ላ​ቸው!


ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።


እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አንተ ሰነፍ! በዚች ሌሊት ነፍ​ስ​ህን ከሥ​ጋህ ለይ​ተው ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ እን​ግ​ዲህ ያጠ​ራ​ቀ​ም​ኸው ለማን ይሆ​ናል? አለው።


跟着我们:

广告


广告