መክብብ 2:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበብንና ዕውቀትን፥ ደስታንም ይሰጠዋል፤ ለኀጢአተኛ ግን በእግዚአብሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛው ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ሥራን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 እርሱም ደስ ለሚያሰኘው ሰው ጥበብንና እውቀትን ደስታንም ይሰጠዋል፥ ለኃጢአተኛ ግን እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጥ ዘንድ እንዲሰበስብና እንዲያከማች ጥረትን ይሰጠዋል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። 参见章节 |