Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




መክብብ 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​መ​በት ድካ​ምና በልቡ ዐሳብ ሁሉ ለሰው አይ​ሆ​ን​ለ​ት​ምና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ሰው ከፀሓይ በታች በሚደክምበት ጥረትና ልፋት ሁሉ ትርፉ ምንድን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከፀሐይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ መጨነቅ የሰው ልጅ ምን ጥቅም ያገኛል?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ታዲያ፥ አስቦና ተጨንቆ በሕይወት ዘመኑ በሚደክምበት ነገር ሁሉ ሰው የሚያተርፈው ቁም ነገር ምንድን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከፀሐይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ አሳብ የሰው ጥቅም ምንድር ነው?

参见章节 复制




መክብብ 2:22
21 交叉引用  

የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።


ሰው በድካሙ ለራሱ ይደክማል፥ ከራሱም ጥፋትን ያርቃል። ጠማማ ግን በአፉ ጥፋትን ይለብሳል።


ከፀ​ሐይ በታች በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?


እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።


ለሠ​ራ​ተኛ የድ​ካሙ ትርፍ ምን​ድን ነው?


በድ​ካ​ምና ነፋ​ስን በመ​ከ​ተል ከሁ​ለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕ​ረ​ፍት ይሻ​ላል።


አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።


ዘመኑ ሁሉ በጨ​ለማ በል​ቅ​ሶና በብዙ ብስ​ጭት በደ​ዌና በኀ​ዘን ነውና።


ከሚ​በ​ላ​ውና ከሚ​ጠ​ጣው፥ ደስም ከሚ​ለው በቀር ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ሌላ መል​ካም ነገር የለ​ው​ምና እኔ ደስ​ታን አመ​ሰ​ገ​ንሁ፤ ይህም ከፀ​ሓይ በታች ከድ​ካሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ለእ​ርሱ የሰ​ጠው ነው።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤


“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?


“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።


ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ።


እና​ን​ተም የም​ት​በ​ሉ​ት​ንና የም​ት​ጠ​ጡ​ትን አት​ፈ​ልጉ፤ ወዲ​ያና ወዲ​ህም አት​በሉ፤ አት​ጨ​ነ​ቁ​ለ​ትም።


እና​ን​ተም እንደ እነ​ዚህ ላሉ​ትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባ​ብሮ ለሚ​ደ​ክም ሁሉ ትታ​ዘ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ።


አንዳችንም ልንወስድ አይቻለንም፤ ምግብና ልብስ ከኖረን ግን እርሱ ይበቃናል።


እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።


跟着我们:

广告


广告