መክብብ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እኔም ጥበብን፥ ሽንገላንና ስንፍናን አይ ዘንድ ተመለከትሁ ፥ ምክርን የሚከተል፥ ምሳሌንስ ሁሉ የሚያደርግላት ሰው ማን ነው? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ከዚያም ጥበብን፣ እብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ሐሳቤን መለስሁ፤ አስቀድሞ ከተደረገው በቀር፣ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ሊያደርግ ይችላል? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 እኔም ጥበብን ዕብደትንና አለማወቅን ለመመርመር ወሰንኩ፥ በፊት የተደረገውን መድገም ካልሆነ በቀር፥ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 መቼም ንጉሥ መሥራት የሚችለው ከእርሱ በፊት የነበሩት ነገሥታት የሠሩትን በመከተል ነው፤ ስለዚህ እኔም ጥበብ፥ ሞኝነትና እብደት ምን እንደ ሆኑ መርምሬ ለማወቅ ማሰብ ጀመርኩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 እኔም ጥበብን ዕብደትንና ስንፍናን አይ ዘንድ ተመለከትሁ፥ በፊት ከተደረገው በቀር፥ ከንጉሥ በኋላ የሚመጣው ሰው ምን ያደርጋል? 参见章节 |