Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 9:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እነ​ር​ሱም በታ​ላቅ ኀይ​ልህ፥ በጸ​ና​ውና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ውም ክን​ድህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ነገር ግን እነርሱ በታላቅ ኀይልህና በተዘረጋች ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በተዘረጋውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸውና።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከዚህም ሁሉ በላይ ይህ ሕዝብ ለራስህ ወገን እንዲሆን የመረጥከውና በታላቁ ኀይልህና ብርታትህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በተዘረጋውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝብህና ርስትህ ናቸው።

参见章节 复制




ዘዳግም 9:29
22 交叉引用  

እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ከግ​ብጽ ምድር ከብ​ረት እቶን ውስጥ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸ​ውና።


“እነ​ዚ​ህም በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በብ​ርቱ እጅህ የተ​ቤ​ዥ​ሃ​ቸው ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህና ሕዝ​ብህ ናቸው።


በዐ​ይኔ ፊት ክፉ ነገ​ርን አላ​ኖ​ር​ሁም፤ ዐመፃ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ጠላሁ።


በአ​ለ​ቆ​ችም ላይ ኀሣር ፈሰሰ፥ መን​ገ​ድም በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ አሳ​ታ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዋሊ​ያ​ዎ​ችን ያጠ​ነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፥ ዛፎ​ች​ንም ይገ​ል​ጣል፤ ሁሉም በመ​ቅ​ደሱ፦ ምስ​ጋና ይላል።


ዓለ​ቱን በም​ድረ በዳ ሰነ​ጠቀ፤ ከብዙ ጥልቅ እን​ደ​ሚ​ገኝ ያህል አጠ​ጣ​ቸው።


የአ​ሕ​ዛብ ወገ​ኖች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፤


አሁ​ንም ቃሌን በእ​ው​ነት ብት​ሰሙ፥ ኪዳ​ኔ​ንም ብት​ጠ​ብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የተ​መ​ረጠ ርስት ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐው​ቅህ ዘንድ በፊ​ት​ህም ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝ​ብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገ​ለ​ጥ​ልኝ” አለው።


“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።


ከጥ​ንት እን​ዳ​ል​ገ​ዛ​ኸን ስም​ህም በእኛ ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ጠራ ሆነ​ና​ልና።


አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አን​ተም ሠሪ​ያ​ችን ነህ፤ እኛም ሁላ​ችን የእ​ጅህ ሥራ ነን።


ምድ​ሪ​ቱን፥ በም​ድር ፊት ላይ ያሉ​ትን ሰዎ​ች​ንና እን​ስ​ሶ​ችን በታ​ላቅ ኀይ​ሌና በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችው ክንዴ ፈጥ​ሬ​አ​ለሁ፤ ለዐ​ይ​ኔም መል​ካም ለሆ​ነው እሰ​ጣ​ታ​ለሁ።


ሕዝቡ ያዕ​ቆ​ብም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ገመድ ነው።


እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ፈጥ​ነህ ውረድ፤ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብህ በድ​ለ​ዋ​ልና፤ ፈጥ​ነው ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና፥ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልም ለራ​ሳ​ቸው አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እን​ዲህ ብዬ ጸለ​ይሁ፦ የአ​ማ​ል​ክት ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልህ የተ​ቤ​ዠ​ሃ​ቸ​ውን፥ በጠ​ነ​ከ​ረ​ች​ውም እጅ​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ከግ​ብፅ ያወ​ጣ​ሃ​ቸ​ውን ሕዝ​ብ​ህ​ንና ርስ​ት​ህን አታ​ጥፋ።


跟着我们:

广告


广告