Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 9:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ከሰ​ማይ በታች እደ​መ​ስስ ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለሚ​በ​ረ​ታና እጅግ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።’

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አጠፋቸውና ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተንም ከእነርሱ ይልቅ ብርቱና ብዙ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አጠፋቸው ዘንድ፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስስ ዘንድ ተወኝ፥ አንተንም ከእነርሱ የበረታና የበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ።’

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እንግዲህ ተወኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ሊያስታውሳቸው በማይችል ሁኔታ ልደምስሳቸው፤ ከዚያም በኋላ አንተን ከእነርሱ ይበልጥ ኀይልና ብዛት ላለው ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አጠፋቸው ዘንድ፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስስ ዘንድ ተወኝ፤ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ ብሎ ተናገረኝ።

参见章节 复制




ዘዳግም 9:14
19 交叉引用  

ትእ​ዛ​ዝ​ህን እና​ፈ​ርስ ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ና​ልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚ​ሠሩ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ጋርም ተጋ​ብ​ተ​ና​ልና ከእኛ ከሞት የሚ​ያ​መ​ልጥ እስ​ከ​ማ​ይ​ኖር ድረስ ፈጽ​መህ አት​ቈ​ጣን።


በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


አሕ​ዛ​ብን ገሠ​ጽህ፥ ዝን​ጉ​ዎ​ችም ጠፉ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደመ​ሰ​ስህ።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


ዘር​ህም እንደ አሸዋ የሆ​ድ​ህም ትው​ልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፤ አሁ​ንም ስምህ ከፊቴ ባል​ጠ​ፋና ባል​ፈ​ረሰ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ለዚህ ሕዝብ ስለ መል​ካም አት​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ፥ ቅን​አ​ቱም በዚያ ሰው ላይ ይነ​ድ​ዳል እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም፤ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈው ርግ​ማን ሁሉ በላዩ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስ​ሰ​ዋል።


እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ፤ ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።


ድል የነሣው እንዲሁ በነጭ ልብስ ይጐናጸፋል፤ ስሙንም ከሕይወት መጽሐፍ አልደመስስም፤ በአባቴና በመላእክቱም ፊት ለስሙ እመሰክርለታለሁ።


跟着我们:

广告


广告