Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 7:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓይ​ንህ እያ​የች፥ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ምል​ክ​ት​ንም፥ ተአ​ም​ራ​ት​ንም፥ የጸ​ና​ች​ው​ንም እጅ፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክንድ አድ​ርጎ እን​ዳ​ወ​ጣህ፤ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ያደ​ር​ጋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ታላላቅ ፈተናዎችን፣ ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ነገሮችን አምላክህ እግዚአብሔር አንተን ያወጣበትን ብርቱ እጅና የተዘረጋች ክንድ በገዛ ዐይንህ አይተሃል። አምላክህ እግዚአብሔር አሁን በምትፈራቸው ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያንኑ ያደርጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን ታላላቅ መቅሠፍቶች፥ ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክህ አንተን ነጻ ያወጣበትን ታላቅ ኀይሉንና ሥልጣኑን አስታውስ፤ ግብጻውያንን ባጠፋበት ዐይነት ዛሬ አንተ የምትፈራቸውን እነዚህንም ሕዝቦች ሁሉ ያጠፋቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አምላክህ እግዚአብሔር፥ ዓይንህ እያየች፥ ታላቅን መቅሠፍት ምልክትንም ተአምራትንም የጸናችውን እጅ የተዘረጋውንም ክንድ አድርጎ እንዳወጣህ፥ አስብ፤ እንዲሁ አምላክህ እግዚአብሔር አንተ በምትፈራቸው በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።

参见章节 复制




ዘዳግም 7:19
14 交叉引用  

ስለ ቅን​ነ​ትና ስለ የዋ​ህ​ነት ስለ ጽድ​ቅም አቅና፥ ተከ​ና​ወን፥ ንገ​ሥም፤ ቀኝ​ህም በክ​ብር ይመ​ራ​ሃል።


በግ​ብጽ ሀገ​ርና በጣ​ኔ​ዎስ በረሃ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት የሠ​ራ​ውን ተአ​ም​ራት።


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ያዩ​አ​ቸ​ውን ታላ​ላ​ቆች ፈተ​ና​ዎ​ችን፥ ታላ​ላ​ቆች ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቆ​ችን አይ​ታ​ች​ኋል።


በዚ​ያም ጊዜ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብዬ አዘ​ዝ​ሁት፦ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ነ​ዚህ በሁ​ለቱ ነገ​ሥት ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አይ​ተ​ዋል፤ እን​ዲሁ በም​ታ​ል​ፍ​ባ​ቸው መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋል።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥


ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው።


እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በዐ​ይ​ና​ች​ንም ፊት እነ​ዚ​ያን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ያደ​ረገ፥ በሄ​ድ​ን​ባ​ትም መን​ገድ ሁሉ፥ ባለ​ፍ​ን​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል የጠ​በ​ቀን፥ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


ኢያ​ሱም አለ፥ “ሕያው አም​ላክ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ፥ እር​ሱም ከፊ​ታ​ችሁ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ፈጽሞ እን​ዲ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በዚህ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


跟着我们:

广告


广告