Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 4:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እግዚአብሔር እናንተን በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚበትናችሁ አሕዛብ መካከል የምትተርፉት ጥቂቶቻችሁ ብቻ ናችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጌታም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ ጌታ በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔር በሌሎች ሕዝቦች መካከል ይበታትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ።

参见章节 复制




ዘዳግም 4:27
23 交叉引用  

እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ።


ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።”


እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።


ደነ​ገጡ፥ እንደ ሰካ​ራ​ምም ተን​ገ​ዳ​ገዱ፥ ጥበ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ተዋጠ።


ንጉሥ ውበ​ት​ሽን ወድ​ዶ​አ​ልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።


የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።


ወይራ በተ​መታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እን​ደ​ሚ​ቀር፥ አራት ወይም አም​ስት በዛ​ፊቱ ጫፍ እን​ደ​ሚ​ገኝ፥ በእ​ርሱ ዘንድ ቃር​ሚያ ይቀ​ራል” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”


ስለ​ዚህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕ​ዛብ አር​ቄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይሁን እንጂ በመ​ጡ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች በእ​ነ​ዚያ ትንሽ መቅ​ደስ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ በል።


በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በም​በ​ት​ና​ቸው ጊዜ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም በም​ዘ​ራ​ቸው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


ደግ​ሞም ወደ አሕ​ዛብ እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም እበ​ት​ና​ቸው ዘንድ በም​ድረ በዳ በእ​ነ​ርሱ ላይ እጄን አነ​ሣሁ።


ወደ አሕ​ዛ​ብም እበ​ት​ን​ሻ​ለሁ፤ በሀ​ገ​ሮ​ችም እዘ​ራ​ሻ​ለሁ፤ ከአ​ን​ቺም ርኵ​ሰ​ትሽ ይጠ​ፋል።


“ሞሳ​ሕና ቶቤል፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃ​ብ​ራ​ቸ​ውም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ነው፤ ሁሉም ሳይ​ገ​ረዙ በሰ​ይፍ ተገ​ድ​ለ​ዋል፤ በሕ​ያ​ዋን ምድር ያስ​ፈሩ ነበ​ርና።


አል​ሰ​ሙ​ት​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ተቅ​በ​ዝ​ባ​ዦች ይሆ​ናሉ።


እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ።


ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን፥ በአ​ን​ተም ላይ የም​ት​ሾ​ማ​ቸ​ውን አለ​ቆ​ች​ህን አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ወዳ​ላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸው ሕዝብ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ በዚ​ያም ሌሎ​ችን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አማ​ል​ክ​ትን ታመ​ል​ካ​ለህ።


ዛሬም እን​ዳሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣና በመ​ቅ​ሠ​ፍት፥ በታ​ላ​ቅም መዓት ከም​ድ​ራ​ቸው ነቀ​ላ​ቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ት​ህን ይቅር ይል​ሃል ይራ​ራ​ል​ህ​ማል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ከበ​ተ​ነ​በት ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል መልሶ ይሰ​በ​ስ​ብ​ሃል።


እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ፤ ከሰ​ዎ​ችም መካ​ከል መታ​ሰ​ቢ​ያ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ።


跟着我们:

广告


广告