Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 34:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ ብዬ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ል​ሁ​ላ​ቸው ምድር ይህች ናት፤ እነ​ሆም፥ በዐ​ይ​ንህ እን​ድ​ታ​ያት አደ​ረ​ግ​ሁህ፤ ነገር ግን ወደ​ዚ​ያች አት​ገ​ባም” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ፣ ‘ለዘሮቻችሁ እሰጣለሁ’ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር ይህች ናት። በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታም፦ “ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፥ በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለዘሮቻቸው አወርሳት ዘንድ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው የተስፋ ምድር ይህች ናት፤ እነሆ፥ እርስዋን በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ወደዚያች መግባት ግን አይፈቀድልህም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም፦ ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማልሁላቸው ምድር ይህች ናት፤ በዓይንህ እንድታያት አደረግሁህ፥ ነገር ግን ወደዚያች አትሻገርም አለው።

参见章节 复制




ዘዳግም 34:4
15 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ።


የም​ታ​ያ​ትን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።


በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ ቆሞ​በት ነበር፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ አት​ፍራ፥ ይህ​ችን አንተ የተ​ኛ​ህ​ባ​ትን ምድር ለአ​ን​ተም ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትቀ​ድ​ሱኝ ዘንድ በእኔ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ምድር ይህን ማኅ​በር ይዛ​ችሁ አት​ገ​ቡም” አላ​ቸው።


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤


እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ግቡ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ይሰ​ጣት ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ውረሱ።


ምድ​ሪ​ቱን ፊት ለፊት ታያ​ለህ እንጂ ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​ገ​ባም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰጠ፤ ወረ​ሱ​አ​ትም፥ ተቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።


የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።


跟着我们:

广告


广告