Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 31:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አላ​ቸ​ውም፥ “እኔ ዛሬ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖ​ኛል፤ ከዚህ በኋላ እወ​ጣና እገባ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ርም’ ብሎ​ኛል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “እነሆ፤ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከእንግዲህ ልወጣና ልገባ አልችልም፤ እግዚአብሔርም ‘ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “እነሆ፤ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከእንግዲህ ልወጣና ልገባ አልችልም፤ ጌታም ‘ዮርዳኖስን አትሻገርም’ ብሎኛል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ የእኔ ዕድሜ መቶ ኻያ ዓመት ስለ ሆነ ከእንግዲህ ወዲህ እናንተን መምራት አይቻለኝም፤ ከዚህም በላይ እኔ ዮርዳኖስን እንደማልሻገር እግዚአብሔር ነግሮኛል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አላቸውም፦ እኔ ዛሬ መቶ ሀያ ዓመት ሆኖኛል፤ ከዚህ በኋላ እወጣና እገባ ዘንድ አልችልም፤ እግዚአብሔርም፦ ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል።

参见章节 复制




ዘዳግም 31:2
17 交叉引用  

የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።


አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።


ፈር​ዖ​ን​ንም በተ​ና​ገ​ሩት ጊዜ ሙሴ ሰማ​ንያ ዓመት ሆኖት ነበር፤ አሮ​ንም ሰማ​ንያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ትቀ​ድ​ሱኝ ዘንድ በእኔ አላ​መ​ና​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ምድር ይህን ማኅ​በር ይዛ​ችሁ አት​ገ​ቡም” አላ​ቸው።


በፊ​ታ​ቸው የሚ​ወ​ጣ​ው​ንና የሚ​ገ​ባ​ውን፥ የሚ​ያ​ስ​ወ​ጣ​ቸ​ው​ንና፥ የሚ​ያ​ስ​ገ​ባ​ቸ​ው​ንም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማኅ​በር እረኛ እን​ደ​ሌ​ለው መንጋ እን​ዳ​ይ​ሆን።”


አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት የሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ፊቴን እን​ደ​ማ​ታ​ዩኝ እኔ ዐው​ቄ​አ​ለሁ።


“አርባ ዓመት ሲሞ​ላ​ውም ወን​ድ​ሞ​ቹን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሊጐ​በ​ኛ​ቸው በልቡ ዐሰበ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤


ሙሴም ይህን ቃል ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ተና​ግሮ ጨረሰ።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።


跟着我们:

广告


广告