Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 3:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ከገ​ለ​ዐ​ድም የቀ​ረ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ባሳ​ንን ሁሉ፥ የአ​ር​ጎ​ብ​ንም ምድር ሁሉ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራ​ፋ​ይም ሀገር ተብላ ተቈ​ጠ​ረች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ቀሪውን የገለዓድ ምድርና የዐግ ግዛት የሆነውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። በባሳን የሚገኘው መላው የአርጎብ ክልል የራፋይማውያን ምድር በመባል ይታወቅ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከገለዓድም የቀረውን የዖግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ግዛት ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፥ ያቺ ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተጠራች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለምናሴ ነገድ እኩሌታም ከገለዓድ የተረፈውንና ዖግ ይገዛው የነበረውን ባሳንን በሙሉ ሰጠሁ፤ ይኸውም መላው የአርጎብ ግዛት መሆኑ ነው።” ባሳን የረፋያውያን ምድር በመባል ይታወቅ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከገለዓድም የቀረውን የዐግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ፥ የአርጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራፋይም አገር ተብላ ተቆጠረች።

参见章节 复制




ዘዳግም 3:13
10 交叉引用  

በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ኮሎ​ዶ​ጎ​ሞ​ርና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ረዐ​ይ​ትን በአ​ስ​ጣ​ሮት ቃር​ና​ይም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን ሰዎ​ች​ንና ኦሚ​ዎ​ስን በሴዊ ከተማ ገደ​ሉ​አ​ቸው፤


በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ሁሉ፥ በአ​ር​ኖን ወንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የጋ​ድ​ንና የሮ​ቤ​ልን የም​ና​ሴ​ንም ሀገር፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን መታ።


የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን፥ የባ​ሳ​ንም ንጉሥ ዐግ ሊወ​ጉን ወጡ​ብን፤ እኛም መታ​ና​ቸው፤


ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወስ​ደን ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገን ሰጠ​ና​ቸው።


“ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።


የም​ናሴ ልጅ ኢያ​ዕር እስከ ጌር​ጋ​ሴና እስከ መካቲ ዳርቻ ድረስ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራጃ ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ች​ንም የባ​ሳ​ንን ምድር እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በስሙ አው​ታይ ኢያ​ዕር ብሎ ጠራ።


በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ያል​ወ​ሰ​ድ​ነው ሀገር የለም፤ በባ​ሳን ያለ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ የአ​ር​ጎ​ብን አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ፥ ስድሳ ከተ​ሞ​ችን ወሰ​ድን።


跟着我们:

广告


广告