Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 29:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 “ምስ​ጢሩ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የተ​ገ​ለ​ጠው ግን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እንከተል ዘንድ ለዘላለም የእኛና የልጆቻችን ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 “ምስጢሩ ለአምላካችን ለጌታ ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ እንድንከተል ለዘለዓለም ለእኛና ለልጆቻችን ነው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “እግዚአብሔር አምላካችን ምሥጢር ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፤ የተገለጡ ነገሮች ግን እኛና ልጆቻችን ልንጠብቃቸው የሚገባን የሕጉ ቃሎች ሁሉ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው።

参见章节 复制




ዘዳግም 29:29
30 交叉引用  

ዮሴ​ፍም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከገ​ለ​ጸ​ለት ሰው በቀር መተ​ር​ጐም የሚ​ችል የለም” ብሎ ለፈ​ር​ዖን መለ​ሰ​ለት።


ሰው​ንም፦ ‘እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ጥበብ ነው፤ ከክፉ መራ​ቅም ማስ​ተ​ዋል ነው’ ” አለው።


ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤ ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።


ነገሩ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም ይሉ ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱም ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሕግን ለር​ዳታ ሰጥ​ቶ​አ​ልና።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር የሚ​ቆም፥ ቃሉን የሚ​ያ​ይና የሚ​ሰማ ማን ነው? ቃሉ​ንስ ያዳ​መጠ፥ የሰ​ማስ ማን​ነው?


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለባ​ሪ​ያ​ዎቹ ለነ​ቢ​ያት ያል​ገ​ለ​ጠ​ው​ንና ያል​ነ​ገ​ረ​ውን ምንም አያ​ደ​ር​ግ​ምና።


እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እስ​ክ​መጣ ይኖር ዘንድ ብወ​ድ​ድስ አን​ተን ምን አግ​ዶህ፤ አንተ ግን ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳብ ማን ያው​ቃል? መካ​ሩስ ማን ነው? እኛ ግን ክር​ስ​ቶስ የሚ​ገ​ል​ጠው ዕው​ቀት አለን።


ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተመ​ለስ፤ እኔም ዛሬ እን​ደ​ማ​ዝ​ዝህ ሁሉ አን​ተና ልጆ​ችህ በፍ​ጹም ልብና በፍ​ጹም ነፍስ ቃሉን ስማ፤


ለል​ጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ረው፤ በቤ​ት​ህም ስት​ቀ​መጥ፥ በመ​ን​ገ​ድም ስት​ሄድ፥ ስት​ተ​ኛም፥ ስት​ነ​ሣም አስ​ተ​ም​ረው።


በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፤ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።


የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።


跟着我们:

广告


广告