Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 29:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ስለ​ዚህ በዚህ የሕግ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን መር​ገም ሁሉ ያመ​ጣ​ባት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በዚ​ህች ምድር ነደደ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ርግማን ሁሉ እስኪያመጣባት ድረስ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ በዚህች ምድር ላይ ነደደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ርግማን ሁሉ እስኪያመጣ ድረስ የጌታ ቁጣ በዚህች ምድር ላይ ነደደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ስለዚህም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ተቈጥቶ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ይህን መቅሠፍት ሁሉ በምድራቸው ላይ አወረደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መርገም ሁሉ ያወርድባት ዘንድ የእግዚአብሔር ቁጣ በዚህች ምድር ነደደ፤

参见章节 复制




ዘዳግም 29:27
14 交叉引用  

በዚያ ጊዜም ሸም​በቆ በውኃ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤ​ልን ይመ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀድ ተክ​ለ​ዋ​ልና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጣ​ቸው ከዚች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ራ​ኤ​ልን ይነ​ቅ​ላል፤ በወ​ን​ዙም ማዶ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የይ​ሁዳ ንጉሥ እን​ዳ​ነ​በ​በው እን​ደ​ዚህ መጽ​ሐፍ ቃል ሁሉ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ለሁ።


ከፊቱ አው​ጥቶ እስ​ኪ​ጥ​ላ​ቸው ድረስ ይህ ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ላይ ሆኖ​አ​ልና፤ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ መታ​ቸው፥ በኤ​ማ​ትም ምድር ባለ​ችው በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው። እን​ዲ​ሁም ይሁዳ ከሀ​ገሩ ተማ​ረከ።


አቤቱ፥ አንተ መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነህና፥ ይቅ​ር​ታ​ህም ለሚ​ጠ​ሩህ ሁሉ ብዙ ነውና።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እና​ንተ፥ “አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደ​ረ​ገ​ብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋ​ች​ሁኝ፥ በሀ​ገ​ራ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት እን​ዳ​መ​ለ​ካ​ችሁ፥ እን​ዲሁ ለእ​ና​ንተ ባል​ሆነ ሀገር ለሌ​ሎች ሰዎች ትገ​ዛ​ላ​ችሁ” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሄደ​ውም የማ​ያ​ው​ቋ​ቸ​ው​ንና የማ​ይ​ጠ​ቅ​ሟ​ቸ​ውን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስላ​መ​ለ​ኩና ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸው፥


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እኔ በፊ​ትህ ያኖ​ር​ሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረ​ከ​ቱና መር​ገሙ በወ​ረ​ደ​ብህ ጊዜ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​በ​ት​ንህ በዚያ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ሆነህ በል​ብህ ዐስ​በው፤


跟着我们:

广告


广告