ዘዳግም 28:67 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)67 ከፈራህበት ከልብህ ፍርሀት የተነሣ፥ በዐይንህም ካየኸው የተነሣ፥ ሲነጋ እንዴት ይመሽ ይሆን? ትላለህ፤ ሲመሽም እንዴት ይነጋ ይሆን? ትላለህ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም67 ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፣ ሲነጋ፣ “ምነው አሁን በመሸ!” ሲመሽ ደግሞ፣ “ምነው አሁን በነጋ!” ትላለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)67 ልብህ በፍርሀት ከመሞላቱና ዐይንህ ከሚያየው የተነሣ፥ ሲነጋ፥ ‘ይመሽ ይሆን?’ ሲመሽ ደግሞ፥ ‘ይነጋ ይሆን?’ ትላለህ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም67 ልብህን በሚሞላው ፍርሀትና በዐይንህ በምታየው አስደንጋጭ ትርኢት ምክንያት፥ ሲነጋ መቼ በመሸልኝ፥ ሲመሽም መቼ በነጋልኝ ትላለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)67 አንተ ስለ ፈራህበት ስለ ልብህ ፍርሃት፥ በዓይንህም ስለምታየው አስተያየት፥ ማለዳ፦ መቼ ይመሻል? ትላለህ፤ ማታም፦ መቼ ይነጋል? ትላለህ። 参见章节 |