Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ የከ​ብ​ት​ህን ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህ​ንም ፍሬ ይበ​ላል፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም፥ የላ​ም​ህ​ንና የበ​ግ​ህ​ንም መንጋ አይ​ተ​ው​ል​ህም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 እስክትጠፋም ድረስ የእንስሳትህን ግልገልና የምድርህን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነ ዘይት፣ የመንጋህን ጥጃ ሆነ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገል አያስቀርልህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬና የምድርህን ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ የእህል፥ የወይን ወይም የዘይት፥ የከብትህን ጥጃ ወይም የበግና ፍየል መንጋህን አይተውልህም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 እነርሱ ከብትህንና ሰብልህን ሁሉ ጠራርገው ስለሚበሉት እስክትሞት ድረስ በራብ ትቸገራለህ። እነርሱ አንተ እስክትጠፋ ድረስ ከእህልህ አንዲት ፍሬ፥ ከከብትህ ጥጃ፥ ከበጎችህ መንጋ ጠቦት ከወይንህና ከወይራ ዛፍህ ቅንጣት ፍሬ እንኳ አያስተርፉልህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 እስክትጠፋ ድረስ የከብትህን ፍሬ የምድርህንም ፍሬ ይበላሉ፤ እስኪያጠፉህም ድረስ እህልን የወይንም ጠጅ ዘይትንም የላምህንና የበግህን ርቢ አይተዉልህም።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:51
13 交叉引用  

የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሠራ​ዊት ሁሉ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን የአ​ን​ባ​ዋን ቅጥር ዙሪ​ያ​ዋን አፈ​ረሱ።


ምድ​ራ​ችሁ ባድማ ናት፤ ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ እር​ሻ​ች​ሁ​ንም በፊ​ታ​ችሁ ባዕ​ዳን ይበ​ሉ​ታል፤ ጠላ​ትም ያጠ​ፋ​ዋል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ገ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በእ​ር​ግጥ ለጠ​ላ​ቶ​ችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህ​ል​ሽን አል​ሰ​ጥም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ትን ወይ​ን​ሽን አይ​ጠ​ጡም፤” ብሎ በጌ​ት​ነ​ቱና በክ​ንዱ ኀይል ምሎ​አል።


በዳ​ር​ቻህ ሁሉ ስላለ ኀጢ​አ​ትህ ሁሉ ፋንታ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ለመ​በ​ዝ​በዝ በከ​ንቱ እሰ​ጣ​ለሁ።


በሜዳ ያለው ተራ​ራዬ ሆይ! ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ሁሉ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ህ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ትህ በድ​ን​በ​ሮ​ችህ ሁሉ ለመ​በ​ዝ​በዝ እሰ​ጣ​ለሁ።


ጤት። በሰ​ይፍ የሞ​ቱት በራብ ከሞ​ቱት ይሻ​ላሉ፤ እነ​ዚህ የም​ድ​ርን ፍሬ አጥ​ተው ተወ​ግ​ተ​ውም ዐል​ፈ​ዋል።


ለም​ድ​ሪ​ቱም ሕዝብ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ​ሚ​ኖሩ ስለ እስ​ራ​ኤል ምድ​ርም እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ኖ​ሩ​ባት ሁሉ በዐ​መፅ ይኖ​ራ​ሉና ምድ​ሪቱ በመ​ላዋ ትጠፋ ዘንድ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውን በች​ግር ይበ​ላሉ፤ ውኃ​ቸ​ው​ንም በድ​ን​ጋጤ ይጠ​ጣሉ።


ስለ​ዚህ እነሆ ርስት አድ​ርጌ ለም​ሥ​ራቅ ልጆች አሳ​ልፌ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን በአ​ንተ ዘንድ ይሠ​ራሉ፤ ድን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ንተ ውስጥ ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወተ​ት​ህ​ንም ይጠ​ጣሉ።


በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ፥ ድካ​ም​ህ​ንም ሁሉ የማ​ታ​ው​ቀው ሕዝብ ይበ​ላ​ዋል፤ አን​ተም ሁል​ጊዜ የተ​ጨ​ነ​ቅህ፥ የተ​ገ​ፋ​ህም ትሆ​ና​ለህ።


ፊቱ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ውን፥ የሽ​ማ​ግ​ሌ​ው​ንም ፊት የማ​ያ​ፍ​ረ​ውን፥ ሕፃ​ኑ​ንም የማ​ይ​ም​ረ​ውን ሕዝብ ያመ​ጣ​ብ​ሃል።


በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታ​መ​ን​ባ​ቸው የነ​በሩ፥ የረ​ዘሙ፥ የጸ​ኑም ቅጥ​ሮች እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ያጠ​ፋ​ሃል፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ሁሉ፥ በደ​ጆች ሁሉ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል።


跟着我们:

广告


广告