Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሰም​ተህ ብት​ጠ​ብ​ቃት፥ ብታ​ደ​ር​ጋ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ ያደ​ር​ግ​ሃል እንጂ ጅራት አያ​ደ​ር​ግ​ህም፤ ሁል​ጊ​ዜም በላይ እንጂ በታች አት​ሆ​ንም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔርም ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም። ዛሬ የምሰጥህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቅ፣ መቼውንም ቢሆን በላይ እንጂ ፈጽሞ በታች አትሆንም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታም ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም። ዛሬ የምሰጥህን የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትታዘዝ በጥንቃቄም ብትጠብቅ ሁልጊዜም በላይ እንጂ እታች አትሆንም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አምላክህ እግዚአብሔር በብዙ ሕዝቦች መካከል እንደ ራስ መሪ ያደርግሃል እንጂ እንደ ጅራት ወደ ኋላ እንድትቀር አያደርግህም፤ ዛሬ እኔ የምሰጥህን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በታማኝነት ብትፈጽም ምንም ዐይነት ውድቀት ሳይደርስብህ ወደፊት ትገሠግሣለህ እንጂ ወደ ኋላ አትቀርም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13-14 ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ዛሬም ካዘዝሁህ ከእነዚህ ቃሎች ወደ ቀኝ ወደ ግራም ፈቀቅ ባትል፥ ታመልካቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት ባትከተል፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም።

参见章节 复制




ዘዳግም 28:13
11 交叉引用  

እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ አድ​ኖ​አል በሉ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ይባ​ር​ክ​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ብዙ ታበ​ድ​ራ​ለህ፤ አንተ ግን አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብ​ንም ትገ​ዛ​ለህ፤ አን​ተን ግን አይ​ገ​ዙ​ህም።


ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ትሆን ዘንድ፥ እር​ሱም እንደ ተና​ገረ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ታላቅ ስምን፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ር​ንም አደ​ረ​ገ​ልህ።”


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ብት​ጠ​ብ​ቅም፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ግ​ሃል።


በአ​ንተ መካ​ከል ያለ መጻ​ተኛ በአ​ንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላ​ለህ።


እርሱ ያበ​ድ​ር​ሃል፤ አንተ ግን አታ​በ​ድ​ረ​ውም፤ እርሱ ራስ ይሆ​ናል፤ አን​ተም ጅራት ትሆ​ና​ለህ።


ነገር ግን ምና​ል​ባት የመ​ጣሁ እንደ ሆነ፥ ሳል​ኖ​ርም ቢሆን በወ​ን​ጌል ሃይ​ማ​ኖት እየ​ተ​ጋ​ደ​ላ​ችሁ በአ​ንድ መን​ፈ​ስና በአ​ንድ አካል ጸን​ታ​ችሁ እን​ደ​ም​ት​ኖሩ አይና እሰማ ዘንድ ሥራ​ችሁ ለክ​ር​ስ​ቶስ ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ገባ ይሁን።


跟着我们:

广告


广告