Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 26:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ርስ​ቱና ሕዝቡ ትሆን ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ዛሬ መር​ጦ​ሃ​ልና፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ፣ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፣ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ በዛሬው ዕለት ተናግሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፥ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ ዛሬ ተናግሮአል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት እነሆ፥ ዛሬ ለእርሱ የተለየህ ውድ ሕዝብ አድርጎ ተቀብሎሃል፤ ትእዛዞቹንም ሁሉ እንድትፈጽም ያዝሃል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም እንደ ሰጠህ ተስፋ ገንዘቡና ሕዝቡ መሆንህን፥ ትእዛዙንም ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥

参见章节 复制




ዘዳግም 26:18
20 交叉引用  

ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝብ አድ​ር​ገህ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ኸ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ አም​ላክ ሆነ​ሃ​ቸ​ዋል።


ሰላ​ምን ከሚ​ጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገ​ሠች።


እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ለእ​ኔም ሕዝብ እን​ድ​ት​ሆኑ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ባር​ነት ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


መታ​ጠ​ቂያ በሰው ወገብ ላይ እን​ደ​ም​ት​ጣ​በቅ፥ እን​ዲሁ ለስም፥ ለመ​መ​ኪ​ያና ለክ​ብር ሕዝብ ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣ​ብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙም።”


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፥ ለእ​ኔም ትሆኑ ዘንድ ከአ​ሕ​ዛብ ለይ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና ቅዱ​ሳን ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ።


በዚያ ዘመን አስገባችኋለሁ፥ በዚያም ዘመን እሰበስባችኋለሁ፣ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር አሕዛብ ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


ብቻ​ውን ጠቢብ ለሆ​ነው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይሁን፤ አሜን።


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በም​ድ​ርም ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን መር​ጦ​አ​ልና።


የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ዛሬም የማ​ዝ​ዝ​ህን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን አድ​ርግ።”


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ፈጽ​መህ ብት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ብት​ጠ​ብ​ቅም፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ግ​ሃል።


የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ብት​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ ለእ​ርሱ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ አድ​ርጎ ያቆ​ም​ሃል።


ዛሬ ለእ​ርሱ ሕዝብ ያደ​ር​ግህ ዘንድ፥ እር​ሱም ለአ​ንተ እንደ ተና​ገረ ለአ​ባ​ቶ​ች​ህም ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እንደ ማለ አም​ላክ ይሆ​ን​ልህ ዘንድ ነው።


እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።


“ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በም​ድር ፊት ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መር​ጦ​ሃ​ልና።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


跟着我们:

广告


广告