Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች በአ​ን​ድ​ነት ቢቀ​መጡ፥ አን​ዱም ልጅ ሳይ​ኖ​ረው ቢሞት፥ የሞ​ተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አት​ሂድ፤ ነገር ግን የባ​ልዋ ወን​ድም ወደ እር​ስዋ ገብቶ እር​ስ​ዋን ያግባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ይኑር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፣ የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ወንድማማቾች በአንድ ርስት ላይ ቢኖሩና አንደኛው ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰብ ውጪ የሆነ ሌላ ሰው ማግባት አይኖርባትም፤ የባልዋ ወንድም እርስዋን በማግባት የዋርሳነት ግዴታውን ይፈጽምላት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፥ ከእርስዋም ጋር ይኑር።

参见章节 复制




ዘዳግም 25:5
11 交叉引用  

ታላ​ቂ​ቱም ታና​ሺ​ቱን አለ​ቻት፥ “አባ​ታ​ችን ሽማ​ግሌ ነው፤ በም​ድ​ርም ሁሉ እን​ዳ​ለው ልማድ ሊገ​ና​ኘን የሚ​ችል ሰው በም​ድር ላይ የለም።


እንዲህም ብለው ጠየቁት “መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሲሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ አለ።


“መምህር ሆይ! ሙሴ “የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሎ ጻፈልን።


እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ ሙሴ፦ ‘ወን​ድሙ ልጅ ሳይ​ወ​ልድ ሚስ​ቱን ትቶ የሞ​ተ​በት ሰው ቢኖር ወን​ድሙ ሚስ​ቱን አግ​ብቶ ለወ​ን​ድሙ ዘር ይተካ’ ሲል ጽፎ​ል​ናል።


ኑኃሚንም አለች፦ ልጆቼ ሆይ፥ ተመለሱ፣ ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ የሚሆኑ ልጆች በሆዴ አሉኝን?


ዛሬ ሌሊት እደሪ፣ ነገም እርሱ ዋርሳ መሆን ቢወድድ መልካም ነው፥ ዋርሳ ይሁን፣ ዋርሳ ሊሆን ባይወድድ ግን፥ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ ዋርሳ እሆንሻለሁ፣ እስኪነጋ ድረስ ተኚ።


አሁንም ከገረዶቹ ጋር የነበርሽበት ቦዔዝ ዘመዳችን አይደለምን? እነሆ፥ እርሱ በዛሬ ሌሊት በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል።


እርሱም፦ ማን ነሽ? አለ። እርስዋም፦ እኔ ባሪያህ ሩት ነኝ፣ ዋርሳዬ ነህና ልብስህን በባሪያህ ላይ ዘርጋ አለችው።


ቦዔዝም፦ እርሻውን ከኑኃሚን እጅ በምትገዛበት ቀን፥ ለሞተው በርስቱ ስሙን እንድታስነሣለት ከምዋቹ ሚስት ከሞዓባዊቱ ከሩት ደግሞ ትገዛለህ አለ።


跟着我们:

广告


广告