Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 23:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት በተ​ሳ​ልህ ጊዜ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ፈጽሞ ይሻ​ዋ​ልና፥ ኀጢ​አ​ትም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና መክ​ፈ​ሉን አታ​ዘ​ግይ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት ከተሳልህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር አጥብቆ ከአንተ ይሻዋልና፣ ኀጢአት እንዳይሆንብህ ለመክፈል አትዘግይ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ለእግዚአብሔር ለጌታ ስእለት በተሳልህ ጊዜ እግዚአብሔር ጌታ ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና ከመክፈል አታዘገይ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ለእግዚአብሔር አምላክህ ስእለት በምታደርግበት ጊዜ ለመስጠት ወይም ለመፈጸም ቃል የገባህበትን ስእለት አታዘግይ፤ እግዚአብሔር አንተ የገባኸውን ቃል እንድትፈጽም ይፈልጋል፤ ስእለትህን ካልፈጸምክ ግን ኃጢአት ይሆንብሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘገይ።

参见章节 复制




ዘዳግም 23:21
24 交叉引用  

ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ ብሎ ስእ​ለት ተሳለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በም​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ ቢጠ​ብ​ቀኝ፥ የም​በ​ላ​ው​ንም እን​ጀራ፥ የም​ለ​ብ​ሰ​ው​ንም ልብስ ቢሰ​ጠኝ፥


ወደ እር​ሱም ትጸ​ል​ያ​ለህ፥ እር​ሱም ይሰ​ማ​ሃል፤ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይሰ​ጠ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።


የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከደም አድ​ነኝ፥ አን​ደ​በ​ቴም በአ​ንተ ጽድቅ ደስ ይለ​ዋል።


የአ​ሕ​ዛብ ማኅ​በር ሁላ​ችሁ፥ በእ​ርሱ ታመኑ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም በፊቱ አፍ​ስሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ታ​ችን ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አስ​ታ​ወ​ስሁ፤ የቀ​ደ​መ​ውን ተአ​ም​ራ​ት​ህን አስ​ታ​ው​ሳ​ለ​ሁና፤


ቍጣ​ዬም ይጸ​ና​ባ​ች​ኋል፤ በሰ​ይ​ፍም አስ​ገ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም መበ​ለ​ቶች፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ድሀ-አደ​ጎች ይሆ​ናሉ።


በአ​ራጣ ባያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ባይ​ወ​ስድ፥ እጁ​ንም ከኀ​ጢ​አት ቢመ​ልስ፥ በሰ​ውና በሰው መካ​ከ​ልም የእ​ው​ነ​ትን ፍርድ ቢፈ​ርድ፥


ሰዎ​ቹም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እጅግ ፈሩ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ስእ​ለ​ት​ንም ተሳሉ።


ከን​ቱ​ነ​ት​ንና ሐሰ​ትን የሚ​ጠ​ብቁ፤ ይቅ​ር​ታ​ቸ​ውን ትተ​ዋል።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


“ደግሞ ለቀደሙት ‘በውሸት አትማል ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ’ እንደተባለ ሰምታችኋል።


ሌዋ​ዊ​ዉም፥ ከአ​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት የለ​ው​ምና፥ በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግም፥ መበ​ለ​ትም መጥ​ተው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ታ​ደ​ር​ገው በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ነው።


ከባ​ዕድ ግን በእ​ርሱ ዘንድ ያለ​ህን ሁሉ መቀ​በል ትች​ላ​ለህ፤ በወ​ን​ድ​ምህ ላይ ያለ​ውን ሁሉ ግን ተው​ለት።


ስለ ተሳ​ል​ኸው ስእ​ለት ሁሉ የአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዪ​ቱን ዋጋና የው​ሻ​ውን ዋጋ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አታ​ቅ​ርብ፤ ሁለ​ቱም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና።


ባት​ሳል ግን ኀጢ​አት የለ​ብ​ህም።


ዮና​ታ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዳ​ዊት ጠላ​ቶች እጅ ይፈ​ል​ገው” ብሎ ከዳ​ዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


跟着我们:

广告


广告