ዘዳግም 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ጸሐፍቱም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ልበ ድንጉጥ ሰው ቢሆን የወንድሞቹን ልብ እንደ እርሱ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ከዚያም አለቆቹ፣ “የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ” በማለት ጨምረው ይናገሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 “ከዚያም አለቆቹ፥ ‘የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞቹም ልብ እንዳይባባ ወደ ቤቱ ይመለስ’ በማለት ጨምረው ይናገሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 “የጦር መሪዎች በሌላም በኩል እንዲህ ብለው ይጠይቁ፥ ‘ወኔ የጐደለው ፈሪ ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? እንዲህ ያለ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እንዲህ ያለ ሰው የሌሎችን ወኔ ያቀዘቅዛል፤’ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አለቆቹም ደግሞ ጨምረው፦ ማንም ፈሪና ድንጉጥ ሰው ቢሆን እርሱ ፈርቶ የወንድሞቹን ልብ ደግሞ እንዳያስፈራ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ ብለው ለሕዝቡ ይናገሩ። 参见章节 |