ዘዳግም 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 “ከተማዪቱን ለመውጋትና ለመውሰድ ብዙ ቀን ብትከብባት፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቍረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቍረጣቸው፤ ወደ አንተ ይመጣና ወደ ቅጥርህም ይገባ ዘንድ የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፣ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቍረጣቸው፤ ከብበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 “አንድን ከተማ ተዋግተህ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ ካደረግህ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፈህ አታጥፋ፤ የእነርሱን ፍሬ መብላት ትችላለህና አትቁረጣቸው፤ ከበህ የምታጠፋቸው የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “አንዲት ከተማ ለመማረክ በምትዘጋጅበት ጊዜ ከበባው ረጅም ጊዜ የወሰደ እንደ ሆነ የዛፎቹ ፍሬ ምግብ ሊሆኑህ ስለሚችሉና ዛፎችም እንደ ሰዎች ከበባ የሚደረግባቸው ስላልሆኑ ዛፎችን አትቊረጥ። የሜዳ ዛፎችን ከበባ የምታደርግባቸው ሰዎች ናቸውን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ከተማይቱን ለመውሰድ በመውጋት ብዙ ቀን ከብበህ ባስጨነቅሃት ጊዜ፥ ምሳርህን አንሥተህ ዛፎችዋን አትቁረጥ፤ ከእነርሱ ትበላለህና አትቁረጣቸው፤ ከብበህ የምታጠፋው የምድር ዛፍ ሰው መሆኑ ነውን? 参见章节 |