Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ይ​ፈ​ስስ፥ በው​ስ​ጥ​ህም የደም ወን​ጀ​ለኛ እን​ዳ​ይ​ኖር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስስና በሚፈስሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆን ይህን አድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስና በሚፈሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆን ይህን አድርግ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህንንም የምታደርገው እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባት ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ንጹሕ ደም እንዳይፈስስና አንተም የደሙ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው።

参见章节 复制




ዘዳግም 19:10
16 交叉引用  

ንጉ​ሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገ​ረህ አድ​ርግ፤ ገድ​ለ​ህም ቅበ​ረው፤ ኢዮ​አ​ብም በከ​ንቱ ያፈ​ሰ​ሰ​ውን ደም ከእ​ኔና ከአ​ባቴ ቤት ታር​ቃ​ለህ።


ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


ጻድ​ቁ​ንም ስለ ገደለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራራ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።


ትዕቢተኛ ዐይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ የጻድቁን ደም የምታፈስስ እጅ፥


እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ለተ​ን​ኮል ይሮ​ጣሉ፤ ደምን ለማ​ፍ​ሰ​ስም ይፈ​ጥ​ናሉ፤ ሰውን ለመ​ግ​ደል ይመ​ክ​ራሉ፤ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አለ።


በሀ​ገ​ራ​ቸው ንጹ​ሑን ደም አፍ​ስ​ሰ​ዋ​ልና በይ​ሁዳ ልጆች ላይ ስለ አደ​ረ​ጉት ግፍ ግብፅ ምድረ በዳ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስም በረሃ ይሆ​ናል።


ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደ​ድህ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ሰው ነፍስ አታ​ጥ​ፋን፤ ንጹሕ ደም​ንም አታ​ድ​ር​ግ​ብን።” አሉ።


ምድ​ርን የሚ​ያ​ረ​ክ​ሳት ደም ነውና የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን ምድር በነ​ፍስ ግድያ አታ​ር​ክ​ሷት። ምድ​ሪ​ቱም በደም አፍ​ሳሹ ደም ካል​ሆነ በቀር ከፈ​ሰ​ሰ​ባት ደም አት​ነ​ጻም።


ዐይ​ን​ህም አት​ራ​ራ​ለት፤ ነገር ግን ንጹ​ሑን ደም ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም፥ በኖ​ር​ህ​ባ​ትም ጊዜ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ንተ በተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁት ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳ​ል​ሻ​ገር፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር እን​ዳ​ል​ገባ ማለ።


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”


跟着我们:

广告


广告