Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 18:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ያ ነቢይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከተ​ና​ገ​ረው ሁሉ ቃሉ ባይ​ደ​ርስ፤ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ባይ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ቃል አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም፤ ነቢዩ በሐ​ሰት ተና​ግ​ሮ​ታ​ልና አት​ስ​ማው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፣ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አንድ ነቢይ በእግዚአብሔር ስም ትንቢት ተናግሮ ቃሉ ሳይፈጸም ቢቀር ያ ትንቢት ነቢዩ በግምት የተናገረው ነው እንጂ ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት የተናገረው ቃል ስላልሆነ ልትፈራው አይገባም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።

参见章节 复制




ዘዳግም 18:22
13 交叉引用  

ሚክ​ያ​ስም፥ “በሰ​ላም ብት​መ​ለስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለም” አለ። ደግ​ሞም አሕ​ዛብ ሁሉ ሆይ! ስሙኝ” አለ።


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ታመመ፤ ለሞ​ትም ደረሰ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


ይምጡ፤ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁ​ንም ይን​ገ​ሩን፤ ልብም እና​ደ​ርግ ዘንድ፤ ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ው​ንም እና​ውቅ ዘንድ፥ የቀ​ደ​ሙት ነገ​ሮች ምን እንደ ሆኑ ንገ​ሩን፤ የሚ​መ​ጡ​ት​ንም አሳ​ዩን።


ዮና​ስም የአ​ንድ ቀን መን​ገድ ያህል ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦ​ስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች አለ።”


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀ​ገሬ ሳለሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ይህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋ​ሽም፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ ከክ​ፉው ነገ​ርም የም​ት​መ​ለስ አም​ላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ወደ ተር​ሴስ ለመ​ኰ​ብ​ለል ፈጥኜ ነበር።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ ማደሪያው ነቅቶአልና ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሆይ፥ በፊቱ ዝም በል።


ነገር ግን ይና​ገር ዘንድ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል በስሜ የሚ​ና​ገር ነቢይ፥ በሌላ አማ​ል​ክት ስም የሚ​ና​ገር ነቢ​ይም፥ እርሱ ይገ​ደል።


በል​ብ​ህም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያል​ተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል እን​ዴት አው​ቃ​ለሁ ብትል፥


ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።


跟着我们:

广告


广告