Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 17:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 መጽ​ሐፉ ከእ​ርሱ ጋር ይኑር፤ ዕድ​ሜ​ው​ንም ሁሉ ያን​ብ​በው። አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ይማር ዘንድ፥ የዚ​ህን ሕግ ቃል ሁሉ፥ ይህ​ች​ንም ሥር​ዐት ጠብቆ ያደ​ርግ ዘንድ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አምላኩን እግዚአብሔርን ማክበር ይማር ዘንድ፣ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዐት በጥንቃቄ ይከተል ዘንድ ከርሱ ጋራ ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 አምላኩን ጌታን ማክበር ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቃቄ እንዲከተል ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይህን መጽሐፍ አጠገቡ በማኖር በዘመኑ ሁሉ ያንብበው፤ ይህንንም ቢያደርግ እግዚአብሔርን ማክበርና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትንም ሕጎችና ደንቦች በጥንቃቄና በታማኝነት መፈጸምን ይማራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19-20 አምላኩን እግዚአብሔርን መፍራት ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ይህችንም ሥርዓት ጠብቆ ያደርግ ዘንድ፥ ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኮራ ከትእዛዙም ቀኝና ግራ እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረጅም ዘመን ይነግሡ ዘንድ መጽሐፉ ከእርሱ ጋር ይኑር፥ ዕድሜውንም ሁሉ ያንብበው።

参见章节 复制




ዘዳግም 17:19
11 交叉引用  

ጸሓ​ፊው ሳፋ​ንም ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕግ መጽ​ሐፍ ሰጥ​ቶ​ኛል” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ብቻ ፈቃዱ የሆነ፥ ሕጉ​ንም በቀ​ንና በሌ​ሊት የሚ​ያ​ስብ፥


መጻ​ሕ​ፍ​ትን መር​ምሩ፤ በእ​ነ​ርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን የም​ታ​ገኙ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልና፤ እነ​ር​ሱም የእኔ ምስ​ክ​ሮች ናቸው።


“እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን ቃሎች በል​ባ​ች​ሁና በነ​ፍ​ሳ​ችሁ አኑሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለም​ል​ክት በእ​ጃ​ችሁ ላይ እሰ​ሩ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን ወደ እኔ ሰብ​ስ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በም​ድር ላይ በሕ​ይ​ወት በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ እኔን መፍ​ራት ይማ​ሩና ለል​ጆ​ቻ​ቸ​ውም ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎ​ኛ​ልና በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ችሁ ጊዜ በፈ​ጣ​ሪ​ያ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ቆማ​ችሁ ንገ​ራ​ቸው።


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


ሙሴም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ እን​ድ​ት​ማ​ሩ​አ​ትም፥ በማ​ድ​ረ​ግም እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቁ​አት ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ የም​ና​ገ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ።


跟着我们:

广告


广告