Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 17:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለ​በ​ትን በሬ ወይም በግ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠዋ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እንከን ወይም ጕድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ በርሱ ዘንድ አስጸያፊ ነውና ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “በአምላክህ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከበሬ ወይም ከበግ ነውር ወይም ጉድለት ያለበትን ለአምላክህ ለጌታ አትሠዋ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ከከብት ወይም ከበግ መንጋዎች መካከል አንዳች ነውር ያለበትን እንስሳ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት አድርገህ አታቅርብ፤ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሠዋ።

参见章节 复制




ዘዳግም 17:1
19 交叉引用  

ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ የደ​ከሙ፥ መል​ካ​ቸ​ውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ሁሉ እንደ እነ​ርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላ​የ​ሁም፤


ነውር የሌ​ለ​በት የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለእ​ና​ንተ ይሁን፤ ከበ​ጎች ወይም ከፍ​የ​ሎች ውሰዱ።


አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ እውነተኛ ሚዛን ግን በእርሱ ዘንድ የተመረጠ ነው።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ሁለት ዐይነት ሚዛንና ሁለት ዐይነት መስፈሪያ፥ ሁለቱ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሳን ናቸው። የሚሠራቸውም በሥራው ይሰነካከላል።


እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ናቸው፥ ሰባተኛውንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤


“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


ዕውር መሥዋዕትንም ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? አንካሳውንና የታመመውን ስታቀርቡ ይህ ክፉ አይደለምን? ያንን ለአለቃህ አቅርብ፣ በውኑ በአንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ፊትህን ይቀበላልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፥ ከላ​ሞች አንድ በሬ፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውም ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


ነው​ረኛ ወይም አን​ካሳ ወይም ዕውር ቢሆን፥ ወይም አን​ዳች ክፉ ነውር ቢኖ​ረው፥ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አት​ሠ​ዋው።


ስለ ተሳ​ል​ኸው ስእ​ለት ሁሉ የአ​መ​ን​ዝ​ራ​ዪ​ቱን ዋጋና የው​ሻ​ውን ዋጋ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አታ​ቅ​ርብ፤ ሁለ​ቱም በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሚ​ያ​ጸ​ይፉ ናቸ​ውና።


የሰ​ደ​ዳት የቀ​ድሞ ባልዋ ከረ​ከ​ሰች በኋላ ደግሞ ያገ​ባት ዘንድ አይ​ገ​ባ​ውም፤ ያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ጠላ ነውና፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ የሰ​ጠ​ህን ምድር አታ​ር​ክስ።


ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ፥ ክፋ​ት​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።


የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።


ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


跟着我们:

广告


广告