Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አን​ተም በግ​ብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አንተም ራስህ በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርህና አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ይህን ትእዛዝ ዛሬ የምሰጥህም በዚሁ ምክንያት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አንተም ራስህ በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክና ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አንተም በግብጽ ምድር ባሪያ እንደ ነበርክና እግዚአብሔር አምላክህ ነጻ ያወጣህ መሆኑን አስታውስ፤ እኔም ዛሬ ይህን ትእዛዝ የማዝህ በዚህ ምክንያት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበርህ አምላክህም እግዚአብሔር እንዳዳነህ አስብ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝዝሃለሁ።

参见章节 复制




ዘዳግም 15:15
17 交叉引用  

ለእ​ርሱ ለራሱ እን​ዲ​ሆን ሕዝ​ብን ይቤዥ ዘንድ ለእ​ርሱ ለራ​ሱም ታላቅ ስምን ያደ​ርግ ዘንድ አሕ​ዛ​ብ​ንና ሰፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን በመ​በ​ተን ከግ​ብፅ በተ​ቤ​ዠ​ኸው ሕዝ​ብህ ፊት ታም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መራው እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ያለ በም​ድር ላይ ምን ሕዝብ አለ?


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤


እና​ንተ ጽድ​ቅን የም​ት​ከ​ተሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የም​ትሹ፥ ስሙኝ፤ የተ​ቈ​ረ​ጣ​ች​ሁ​በ​ትን ጽኑዕ ዓለት የተ​ቈ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ባ​ት​ንም ጥልቅ ጕድ​ጓድ ተመ​ል​ከቱ።


ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


በእ​ር​ሱም እንደ ቸር​ነቱ ብዛት በደሙ ድኅ​ነ​ትን አገ​ኘን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ተሰ​ረ​የ​ልን።


ያን​ጊዜ ክር​ስ​ቶ​ስን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕግ የተ​ለ​ያ​ችሁ ነበ​ራ​ችሁ፤ ከተ​ስ​ፋው ሥር​ዐ​ትም እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ችሁ፤ ተስ​ፋም አል​ነ​በ​ራ​ች​ሁም፤ በዚ​ህም ዓለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር።


እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ቸሮ​ችና ርኅ​ሩ​ኆች ሁኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በክ​ር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ።


ነገር ግን ከበ​ጎ​ችህ፥ ከእ​ህ​ል​ህም፥ ከወ​ይ​ን​ህም መጭ​መ​ቂያ ስንቅ ትሰ​ን​ቅ​ለ​ታ​ለህ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከህ መጠን ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።


እርሱ ግን አን​ተ​ንና ቤት​ህን ስለ ወደደ፥ በአ​ን​ተም ዘንድ መኖር መል​ካም ስለ​ሆ​ነ​ለት፦ ‘አል​ወ​ጣም’ ቢል፥


አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ ዐስብ፤ ይህ​ንም ሥር​ዐት ጠብቅ፤ አድ​ር​ገ​ውም።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።


跟着我们:

广告


广告