Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በልግስና ስጠው፤ ስትሰጠውም ልብህ አይጸጸት፤ ከዚህም የተነሣ አምላክህ እግዚአብሔር በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይልቅስ ያለ ቅሬታ በለጋስነት በልግስና ስጠው፤ ከዚህም የተነሣ ጌታ አምላክህ በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይልቅስ ያለ ቅርታ በለጋሥነት ስጥ፤ ይህን ብታደርግ አምላክህ እግዚአብሔር በምትሠራው ሥራና በምታደርገው ድርጊት ሁሉ ይባርክሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እጅህን በምትጥልበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ስለዚህ በሥራህ ሁሉ ይባርክሃልና ፈጽመህ ስጠው፥ በሰጠኸውም ጊዜ በልብህ አትጸጸት።

参见章节 复制




ዘዳግም 15:10
21 交叉引用  

ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።


እን​ጀ​ራ​ህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገ​ኝ​ኘ​ዋ​ለ​ህና።


ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።


ከም​ግ​ብ​ህም ለተ​ራበ ብታ​ካ​ፍል፥ የተ​ራ​በች ሰው​ነ​ት​ንም ብታ​ጠ​ግብ፥ ያን​ጊዜ ብር​ሃ​ንህ በጨ​ለማ ይወ​ጣል፤ ጨለ​ማ​ህም እንደ ቀትር ይሆ​ናል።


ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፤’ ይላቸዋል።


በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።”


የሚ​መ​ክ​ርም በመ​ም​ከሩ ይትጋ፤ የሚ​ሰ​ጥም በል​ግ​ስና ይስጥ፤ የሚ​ገ​ዛም በት​ጋት ይግዛ፤ የሚ​መ​ጸ​ው​ትም በደ​ስታ ይመ​ጽ​ውት።


የሚ​በ​ር​ሩም አዕ​ዋፍ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ሉ​ምና ከእ​ነ​ርሱ አት​ብሉ፤


ሌዋ​ዊ​ዉም፥ ከአ​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት የለ​ው​ምና፥ በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግም፥ መበ​ለ​ትም መጥ​ተው ይበ​ላሉ፤ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤ ይኸ​ውም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ታ​ደ​ር​ገው በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ነው።


እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ ርስት አድ​ርጎ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና በመ​ካ​ከ​ልህ ድሃ አይ​ኖ​ርም፤


ለእ​ን​ግ​ዳው በወ​ለድ አበ​ድር፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት በም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክህ ዘንድ ለወ​ን​ድ​ምህ በወ​ለድ አታ​በ​ድር።


“የእ​ር​ሻ​ህን መከር ባጨ​ድህ ጊዜ ነዶም ረስ​ተህ በእ​ር​ሻህ ብታ​ስ​ቀር፥ ትወ​ስ​ደው ዘንድ አት​መ​ለስ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ባ​ር​ክህ፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመ​በ​ለ​ትም ተወው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል።


ነገር ግን ለድ​ሆች መራ​ራ​ትን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መተ​ባ​በ​ርን አት​ርሱ፤ እን​ዲህ ያለው መሥ​ዋ​ዕት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ያሰ​ኘ​ዋ​ልና።


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告