Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 12:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ የማ​ዝ​ዝ​ህን እነ​ዚ​ህን ቃሎች ሁሉ ሰም​ተህ ጠብቅ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፣ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘላለም መልካም እንዲሆንላችሁ፣ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በአምላክህ በጌታ ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፥ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘለዓለም መልካም እንዲሆንላችሁ፥ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘለዓለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቅ፤ ይህንንም ስታደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን ነገርን ማድረግህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርግ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዝህን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምተህ ጠብቅ።

参见章节 复制




ዘዳግም 12:28
15 交叉引用  

የሐ​ማ​ትም ሰዎች አሲ​ማ​ትን ሠሩ፤ አዋ​ው​ያ​ንም ኤል​ባ​ዝ​ር​ንና ተር​ታ​ቅን ሠሩ፤ የሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም ሰዎች ለሴ​ፌ​ር​ዋ​ይም አማ​ል​ክት ለአ​ድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ለአ​ኔ​ሜ​ሌክ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ይሠዉ ነበር።


አን​ተም ደግሞ አባ​ትህ ዳዊት እንደ ሄደ በፊቴ ብት​ሄድ፥ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥


“አቤቱ የሰ​ማይ አም​ላክ ሆይ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ህና ትእ​ዛ​ዝ​ህን ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ ታላ​ቅና የተ​ፈ​ራህ አም​ላክ ሆይ፥


ለእ​ነ​ር​ሱም ኪዳ​ኑን አሰበ፥ እንደ ምሕ​ረ​ቱም ብዛት አዘ​ነ​ላ​ቸው።


በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ።


የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤


“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።


ሕጌን ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


የም​ት​ወ​ዱኝ ብት​ሆኑ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ እኔ የአ​ባ​ቴን ትእ​ዛዝ እንደ ጠበ​ቅሁ፥ በፍ​ቅ​ሩም እን​ደ​ም​ኖር እና​ን​ተም ትእ​ዛ​ዜን ብት​ጠ​ብቁ በፍ​ቅሬ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


እና​ን​ተስ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን ሁሉ ካደ​ረ​ጋ​ችሁ ወዳ​ጆች ናችሁ።


እና​ንተ ግን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ቃል ፈጽ​ማ​ችሁ ንጹ​ሓን ናችሁ።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ምና ጥሩ የሆ​ነ​ውን ነገር ስታ​ደ​ርግ ለአ​ንተ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ አት​ብ​ላው።


“ስለ ለምጽ ደዌ ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያስ​ተ​ማ​ሩ​ህን ሁሉ ፈጽ​መህ እን​ድ​ት​ጠ​ብቅ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ግም ተጠ​ን​ቀቅ፤ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ውን እን​ዲሁ ታደ​ርግ ዘንድ ጠብቅ።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አ​ትም ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ባዘ​ዛ​ችሁ መን​ገድ ሁሉ ሂዱ።”


跟着我们:

广告


广告