ዘዳግም 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩባቸውን፥ በረዥም ተራሮች፥ በኮረብቶችም ላይ ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉት፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረዣዥም ተራሮች፣ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረጅሙ ተራሮች፥ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በምትወርሱአት ምድር የሚኖሩ ሕዝቦች በተራሮች፥ በኮረብቶችና በለመለሙ ዛፎች ሥር ለአማልክታቸው የሚሰግዱባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ደምስሱ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩባቸውን በረጅም ተራሮች በኮረብቶችም ላይ ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው፤ 参见章节 |