Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በም​ድር ላይ የሰ​ማ​ይን ዘመን ያህል ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ዘመ​ና​ችሁ የል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ዘመን ይረ​ዝም ዘንድ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ይህን ካደረጋችሁ፣ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ይህን ካደረጋችሁ፥ ጌታ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ይህን ብታደርግ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል በገባላቸው ምድር የአንተና የልጆችህ ዘመን ከምድር በላይ እንዳለው ሰማይ ይረዝማል።

参见章节 复制




ዘዳግም 11:21
13 交叉引用  

በድ​ካ​ምም ጠላት አል​ሆ​ኑም። ከሰው ጋርም አል​ተ​ገ​ረ​ፉም።


ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።


ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜን ሰላምንም ይጨምሩልሃልና።


ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤ የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል፥ የሕይወትህ መንገድ ይበዛ ዘንድ።


በዚህ ሥርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ፥ የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።


ከዚ​ያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚ​ኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድ​ሜ​ውን ያል​ፈ​ጸመ ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም፤ ጐል​ማ​ሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞ​ታ​ልና፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተ​ረ​ገመ ይሆ​ና​ልና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ር​ሱና ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ላይ ዕድ​ሜ​ያ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘህ አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ላይ ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ።


እና​ንተ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ች​ሁም በዕ​ድ​ሜ​አ​ችሁ ሁሉ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈር​ታ​ችሁ እኔ ለእ​ና​ንተ ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ ዕድ​ሜ​አ​ች​ሁም ይረ​ዝም ዘንድ፤


በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።


跟着我们:

广告


广告