ዘዳግም 11:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 “እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፤ በዐይኖቻችሁም መካከል እንደማይንቀሳቀስ ይሁኑ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 እነዚህን ቃሎቼን፣ በልባችሁና በአእምሯችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግንባራችሁም ላይ ይሁኑ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 “እነዚህን ቃሎቼን፥ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፥ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 “እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር በልቡናችሁና በአእምሮአችሁ ቅረጹአቸው፤ መታሰቢያም ይሆኑላችሁ ዘንድ እነርሱን በክንዳችሁ ላይ እሰሩ፤ በግንባራችሁም ላይ እንደማስታወሻ አኑሩአቸው፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁኑ። 参见章节 |