Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘዳግም 1:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 በፊ​ትህ የሚ​ቆም የነዌ ልጅ ኢያሱ እርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባል፤ እር​ሱን አበ​ር​ታው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድ​ሪ​ቱን ያወ​ር​ሳ​ልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ረዳትህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ይገባባታል፤ ምድሪቱን እንዲወርሱ እስራኤልን የሚመራ እርሱ ስለ ሆነ፣ አበረታታው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በፊትህ የሚቆመው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፤ እርሱ ለእስራኤል ምድሪቱን ያወርሳልና አበረታታው።’

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ነገር ግን የአንተ ረዳት የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደ ምድሪቱ ይገባል፤ ምድሪቱን ይወርሱ ዘንድ እስራኤልን የሚመራ እርሱ ስለ ሆነ አበረታታው።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በፊትህ የሚቆም የነዌ ልጅ ኢያሱ እርሱ ወደዚያ ይገባል፤ እርሱ ለእስራኤል ምድሪቱን ያወርሳልና አደፋፍረው።

参见章节 复制




ዘዳግም 1:38
20 交叉引用  

ሙሴም ከኢ​ያሱ ጋር ተነሣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ራም ወጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ነ​ጋ​ገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነ​ጋ​ገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመ​ለስ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ል​ጋዩ ብላ​ቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድ​ን​ኳኑ አይ​ወ​ጣም ነበር።


ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም።


እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚ​መ​ጡት ከለ​ዳ​ው​ያን ፊት እቆም ዘንድ በመ​ሴፋ እኖ​ራ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ወይ​ኑ​ንና ፍሬ​ውን፥ ዘይ​ቱ​ንም አከ​ማቹ፤ በየ​ዕ​ቃ​ች​ሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያ​ዛ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​መጡ።”


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ሙሴ የላ​ካ​ቸው ሰዎች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው። ሙሴም የነ​ዌን ልጅ አው​ሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።


ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር በእ​ር​ስዋ አስ​ቀ​ም​ጣ​ችሁ ዘንድ እጄን ዘር​ግቼ ወደ ማል​ሁ​ላ​ችሁ ምድር በእ​ው​ነት እና​ንተ አት​ገ​ቡም።


ነገር ግን ምድ​ሪ​ቱን ሊሰ​ልሉ ከሄዱ ሰዎች የነዌ ልጅ ኢያ​ሱና የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ በሕ​ይ​ወት ኖሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እነ​ርሱ፥ “በእ​ው​ነት በም​ድረ በዳ ይሞ​ታሉ” ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና። ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ፥ ከነ​ዌም ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው ስንኳ አል​ቀ​ረም።


“ምድ​ሪ​ቱን ርስት አድ​ር​ገው የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ላ​ችሁ ሰዎች ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ።


ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻ​ገ​ራ​ልና፥ አን​ተም የም​ታ​ያ​ትን ምድር እርሱ ያወ​ር​ሳ​ቸ​ዋ​ልና ኢያ​ሱን እዘ​ዘው፤ አደ​ፋ​ፍ​ረ​ውም፥ አጽ​ና​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የም​ት​ሞ​ት​በት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያ​ሱን ጠር​ተህ እር​ሱን አዝ​ዘው ዘንድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያ​ሱም ሄደው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ቆሙ።


የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ታገ​ባ​ለ​ህና ጽና፤ በርታ፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል” ብሎ አዘ​ዘው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሙ​ሴን አገ​ል​ጋይ የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።


ሳኦ​ልም ወደ እሴይ፥ “በዐ​ይኔ ሞገስ አግ​ኝ​ቶ​አ​ልና ዳዊት በፊቴ እባ​ክህ ይቁም፥” ብሎ ላከ።


跟着我们:

广告


广告